ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2015 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ባሻ አሸብር በአሜሪካ

ምስል
  ደማሙ ብዕረኛ መንግስቱ ለማ ************************** የዛሬ አስር አመት በታላቅ ሹመት                            አሜሪካ ልኮኝ ነበረ መንግስት ዋሽንግተን ገብቼ ዋልኩ አደርኩኝና ሽር ሽር ስል ሳለ ባንድ አውራ ጎዳና አላፊ አግዳሚውን ጥቁሩን ነጩን ሳለ ስመለከተው በኢትዮጵያዊ አይን የውሀ ጥም ደርሶ ስላረገኝ ቅጥል ከመንገድ ዳር ካለች ካንድ ትንሽ ሆቴል ጎራ አልኩና ገና ከወንበር ላርፍ ስል ተንደርድሮ መጣ የሆቴሉ ጌታ አማረው ቋመጠ ከጀለው ሊማታ አብዷል ሰክሯል እንዴ ምንድን መሆኑ ነው በል ንካኝ በዱላ ግንባርህን ላቡነው ብዬ ስነጋገር ሰምቶ ባማርኛ አሳላፊው ሆነ አስታራቂ ዳኛ ለጥ ብሎ እጅ ነሳና እንደሀገራችን ህግ አክብሮ ጠየቀኝ ምን እንደምፈልግ እኔም ጎራ ያልኩንት የሚጠጣ ነገር ለመሻት መሆኑን ነግሬ ከወንበር ይቅርታዎን ጌታ አዝናለሁ በጣሙ ምናምኒት የለም በከንቱ አይድከሙ አለና እጅ ነሳኝ ሳቁን እየቻለ “ውሀም የለ?” ብለውማ በሳቅ ገነፈለ ቤቱን የሞላው ሰው ሁሉም አጨብጭቦ ብራቮ! ተባለ ብራቮ! ብራቮ!  በጣም ተገርሜ ደንቆኝ አየሁት ከዘራዬን ይዤ ሄድኩኝ ወጣሁት ሃሣብ ገብቶኝ ደጅ ሳሰላስል ቆሜ ያን ቂዛዛ መስኮት ባስተውለው አግድሜ አራዳ ግሪኮች እንደሚሸጡት ያለ በያይነቱ አየሁኝ ብስኩት ትዝ አለኝ “አራዳ አዲስአባ ሆይ ሀገርም እንደሰው ይናፍቃል ወይ?” አስጎመጀኝ በሉ ሳይርበኝ ጠግቤ አስተውለው ጀመረ መስኮቱን ቀርቤ ...