ቅዳሜ, ጁላይ 31, 2021

ጌታቸው ጋዲሳ__ኢትዮጵያ

 


የናፍቆት ትዝታሽ ካለን በሕይወት፣ ፍፁም የማንረሳሽ ውድ አገር እናት፤ ይኽ ነው አይባልም ክብር ኩራታችን፣ በነፃነት ስንኖር በኢትዮጵያዊነታችን 🎵🎵🎵 ያብሮ አደግ ያብሮ አደግ ጓደኛ... ጓደኛ ትዝታው አይለቀን፣ ሜዳው ሸንተረሩ ሁሌ 'ሚናፍቀን፤ ናፍቆቱ ያደግንበት መንደር ... መንደር መቼ ይረሳና፣ ሌት ተቀን ብንባዝን ማን እንዳንቺ አለና፣

ክፉ አይንካሽ ሁኚ ደህና ክፉ አይንካሽ ሁኚ ደህና። 🎵🎵🎵


የምሽት የንጋት ነፋሻ አየር፣ ከልብ የሚወደድ የሚፈቀር፤ በአእዋፋት ዝማሬ ታጅቦ፣ ሌሊቱ ነጋ ... ነጋ በፍቅር ታጅቦ፣ ተውቦ። ወግና በዓሉ ያገራችን፣
ውዳመት የሰንበት ኅብረታችን፤

የክረምት የበጋ፣ ባለፀጋ፣ ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ ... ሸጋ። 🎵🎵🎵 ውዲቷ እናት ዓለም ለኛ ... ለኛ ምትክ የሌለሽ፣ ከአይምሮ አይጠፋም ያንቺ ትዝታሽ፤ በፍቅር አየርና ምድርሽ ... ምድርሽ ለሁሉ 'ሚስማማ፣

የደግ ምሳሌ ውብ ዓለም እማማ፤ ምድርሽ ደጉ የሚለማ የደግ ምሳሌ ውብ ዓለም እማማ፤ ምድርሽ ደጉ የሚለማ። 🎵🎵🎵


ብዙ ውለታን አለሽ በልጆችሽ፣ መኖር እንመርጣለን ሳንለይሽ፤ ፍቅርሽ በልባችን የሚኖር፣ ማንም አይለየን ካንቺ ከሞት በቀር ... በቀር። የአያት የቅድመ አያት ታላቅ ቅርስ፣ ጎራዴ ጋሻቸው ሲታወስ፤ በቅኝ ያልተገዛሽ መሬታችን፣ ነፃነት ነው ክብራችን፣ የጀግንነታችን። ወግና በዓሉ ያገራችን፣ ያውዳመት የሰንበት ኅብረታችን፤ የክረምት የበጋ፣ ባለፀጋ፣ ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ



ማክሰኞ, ሜይ 18, 2021

«የሬዲዮ ቀን»ን የማያከብሩት ሬዲዮ ጣቢያዎች


አንተነህ ቸሬ

በየዓመቱ የካቲት 13 (እ.አ.አ) የዓለም የሬዲዮ ቀን (World Radio Day) ተከብሮ ይውላል ።የዓለም የሬዲዮ ቀን ሬዲዮ ለዓለም ያበረከተውንና እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ የማሰብና የሬዲዮን ልዩ ገፅታዎች/ባህርያት የማስገንዘብ ዓላማ አለው ።

በዕለቱ ሬዲዮ ከሌሎቹ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎች ስለሚለይባቸውና ተመራጭ ስለሚሆንባቸው ባህርያቱ እንዲሁም ሬዲዮ ለዓለም ሕዝብ ስላበረከታቸው አስተዋፅኦዎችና ስለዋላቸው ውለታዎች በስፋት የሚነገርበትና የሚዘመርበት ነው ።ሬዲዮ ያሉበትን ውስንነቶች ስለማሻሻልና ስላጋጠሙት ችግሮችም ይመከራል ።

እ.አ.አ በ2010 የስፔን የሬዲዮ አካዳሚ (Span­ish Radio Academy) ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀን (World Radio Day) እንዲሰየም ለአገሪቱ መንግሥት ጥያቄ አቀረበ ።የስፔን መንግሥትም የአካዳሚውን ጥያቄ ተቀብሎ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (UNESCO) አቀረበ ።

የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ለተቋሙ ጠቅላላ ጉባዔ ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሠረት የካቲት 13 (እ.አ.አ) የዓለም የራዲዮ ቀን ሆኖ በየዓመቱ እንዲከበር እ.አ.አ በ2011 ውሳኔ አስተላለፈ ።ቀኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሬዲዮ (UN Radio) ከተቋቋመበት ቀን (እ.አ.አ የካቲት 13 ቀን 1946 ዓ.ም) ጋር ይገጣጠማል ።


የመጀመሪያው የዓለም የሬዲዮ ቀን የተከበረው እ.አ.አ በ2012 ሲሆን በወቅቱ በእንግሊዝ፣ በስፔን፣ በስዊዘርላንድ፣ በኢጣሊያ፣ በባንግላዴሽና በሌሎች አገራት በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተከብሮ ነበር ።በጊዜው አንዳንድ አገራት የቀኑን አከባበር የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ ልዩ ኮሚቴዎችንም አቋቁመው ነበር ።

የተለያዩ አገራት ቀኑን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ያከብሩታል ።በሬዲዮ ጣቢያዎች ከሚነገሩ መልዕክቶች ጀምሮ የአገራቱ መሪዎች እስከሚካፈሉባቸው ትልልቅ መሰናዶዎች ድረስ የዘለቁ ዝግጅቶች የቀኑ ማጀቢያና ማድመቂያ ይሆናሉ ።

ከሬዲዮ በተጨማሪ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ጋዜጦችና መጽሔቶችም ለዓለም የሬዲዮ ቀን ትኩረት ሰጥተው ልዩ ልዩ ዘገባዎችን ያስተላልፋሉ፤ ያስነብባሉ ።የትምህርትና የምርምር ተቋማት ውይይቶችን እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተቋማት ደግሞ በዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብሮችን ያዘጋጃሉ ።

የዓለም የሬዲዮ ቀንን በቀላሉ የማይመለከቱት የአገራት መሪዎችም አሉ ።ለአብነት ያህል የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀንን በማስመልከት መልዕክት የማስተላለፍ ልማድ አላቸው ።

ሬዲዮ ለዓለም ታላቅ ባለውለታ እንደሆነም ይመሰክራሉ ።ሕንድ በሬዲዮ ጣቢያዎች ቁጥር በግንባር ቀደምትነት ከሚሰለፉ አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ልብ ይሏል ።

ዘንድሮም የዓለም የሬዲዮ ቀን ለ10ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን የዘንድሮው የሬዲዮ ቀን ለውጥ፣ ፈጠራ እና ትስስር የሚሉ ዋና ዋና ጽንሰ ሃሳቦችን ያነገበና ያስተጋባ ሆኗል ።ዘንድሮ የዓለም የሬዲዮ ቀንን ለሁለተኛ ጊዜ ያከበረችው ኢትዮጵያም ቀኑን ካከበሩ አገራት መካከል ተመድባለች ።

የዓለም የሬዲዮ ቀን በኢትዮጵያ በይፋ መከበር የጀመረው ባለፈው ዓመት ነው ።በወቅቱ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አስተባባሪነት የሀገሪቱ የብሮድካስት ባለሥልጣናት፣ አንጋፋ ጋዜጠኞችና ምሁራንን በተገኙበት ቀኑ ተከብሯል ።ዘንድሮም በዓሉ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና በዩኔስኮ ትብብር ለሁለተኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን ለአንጋፋ ጋዜጠኞች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል ።ቀኑ የተከበረው ከኢትዮጵያ ሬዲዮን 85ኛ እንዲሁም ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ጣቢያ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር ተቆራኝቶ ነው ።

 ለዛሬው ትዝብቴ መነሻ የሆነኝ ይኸው የዓለም የሬዲዮ ቀን አከባበር ጉዳይ ነው ።በርካቶች ባለውለታቸውን ሲዘክሩ የእኛ አገር ‹‹ሬዲዮ ጣያዎች›› ግን ለዚህ አልታደሉም ።ይህ የሬዲዮ ውለታ የሚነገርበት፣ ተመራጭነቱና ተደራሽነቱ የሚወሳበት እንዲሁም ስለተግዳሮቶቹና ስለቀጣይ ጉዞዎቹ የሚመከርበት ቀን በሀገራችን ሬዲዮ ጣቢያዎች ሳይከበርና ሳይታወስ ቀርቷል ።

በእርግጥ ቀኑ ይፋዊ በሆነ መልኩ መከበር ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኩል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲደረግ ይስተዋላል ።‹‹ሸገር ኤፍ ኤም 102.1›› ሬዲዮ ጣቢያ ቀኑን በማስታወስና በማክበር ረገድ ከሌሎቹ የአገሪቱ ሬዲዮ ጣቢዎች ሁሉ የተሻለ ቁመና አለው ።እንዲያው ይህ ጣቢያ ብቻ የሬዲዮን ቀን ሲዘክር የሰማ ሰው ‹‹ሸገር ብቻ ነው እንዴ ሬዲዮ ጣቢያ›› ብሎ ቢጠይቅ አይፈረድበትም ።

ብዙዎቹ ሬዲዮ ጣቢያዎች የካቲት 13 የዓለም የሬዲዮ ቀን ስለመሆኑ የሚያውቁትና የሚሰሙት ከፌስቡክ ወይም ከሌላ ጣቢያ ነው ።ቀደም ብሎ በመዘጋጀት ቀኑን ለማክበር የሚደረግ ዝግጅትም ሆነ ፍላጎት የላቸውም ።

‹‹ዛሬ የዓለም የሬዲዮ ቀን እንደሆነ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተመልክተናል›› በሚል የሰነፍ ወሬ ጀምረው ‹‹ሬዲዮ እጅግ ጥሩና ተወዳጅ ሚዲያ ነው›› በሚል ‹‹ወተት ነጭ ነው›› ይዘት ያለው አስቂኝ ‹‹መረጃ›› ቀኑን የመዘከር ሥራቸውን ይቋጫሉ ።ወሳኝ ከሆነው የሬዲዮ ቀን ይልቅ ፋይዳቸው እዚህ ግባ ለማይባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ቅድሚያ ይሰጣሉ ።

ኢትዮጵያ ከሬዲዮ ጋር የተዋወቀችው ከበርካታ የአፍሪካና የእስያ አገራት ቀድማ ነው ።በ1928 ዓ.ም የተጀመረው ይኸው አገልግሎት ዘመኑ ከሚደርስበት የቴክኖሎጂ መሻሻል ጋር እየተለዋወጠ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል ።ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የሬዲዮ

 ትዝታ አላቸው ።ግዙፍ ከሆኑ የአገሪቱ ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክስተቶች ጋር የሚነሱ የሬዲዮ ትዝታዎች ዛሬም ድረስ በብዙዎች ይታወሳሉ ።የአንጋፋ የኪነ ጥበብ፣ የሥነ-ጽሑፍና የፖለቲካ ሰዎች ድምፆች/ሥራዎች ሬዲዮን ያስታውሱናል ።

ግማሽ ክፍለ ዘመንን ተሻግረው ዛሬም ድረስ የሚታወሱ ሥራዎችን ከሬዲዮ ነጥሎ ማሰብ አይቻልም ።ጊዜ የከዳው መንግሥት ከዙፋኑ መውረዱ/መባረሩና ባለጊዜው ወንበር መያዙ የተነገረው በሬዲዮ ነው፤ ትልልቅ አገራዊ ውሳኔዎች ለሕዝብ የተገለፁት በሬዲዮ ነው፤ ጆሮ የሚይዙ የድል ዜናዎች የተበሰሩትና አንገት ያስደፉ የመርዶ ወሬዎች የተነገሩትም በሬዲዮ ነው ።

በኢትዮጵያ ከ85 ዓመታት በፊት የተጀመረው የሬዲዮ ስርጭት ብዙ የሬዲዮ ጣቢያዎችን ወልዷል ።በአሁኑ ወቅት ዝግጅቶቻቸውን ከ60 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች የሚያሰራጩ ከ75 በላይ የሬዲዮ ጣቢያዎች አሉ ።

ከ100 ሚሊዮን የሚበልጥና ሰፊ የቋንቋ፣ የባሕል፣ የአመለካከትና የታሪክ ብዝሃነት ያለው ሕዝብ ላላት አገር ይህ ቁጥር በጣም ጥቂት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ያሉት ጣቢያዎች እንኳ ቀኑን በውል አለመዘከራቸውና አለማስታወሳቸው ‹‹ቁም ነገሩ ከቁጥሩ ማነስና መብዛት አይደለም›› እንድንል ያደርገናል ።

ሬዲዮ ከታወቀበትና ወደሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያበረከተውን አስተዋፅኦና የተጫወተውን ሁለንተናዊ ሚና ማወደስ፣ የሬዲዮ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍን ማጠናከር፣ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጎልበት፣ የሰዎችን መረጃ የማግኘት መብትንና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን ማፅናት፣ ስለሬዲዮ ጣቢያዎች ተደራሽነት፣ መስፋፋትና መጠናከር እንዲሁም ስለዘርፉ ችግሮች መምከር፣ በሬዲዮ ጋዜጠኝነት የሥነ-ምግባር ደንቦች ላይ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር፣ መንግሥታት ለሬዲዮ ዘርፍ መጠናከር ድጋፍ

 እንዲያደርጉ ማሳሰብ እንዲሁም ሕዝብ ሬዲዮን እንዲጠቀም ማበረታታት ቀኑ ከሚከበርባቸው ዓላማዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ።ይሁን እንጂ የእኛ አገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ግን እነዚህን ዓላማዎች ያነገበው ቀን መከበር ግድ ሲሰጣቸው አይስተዋልም ።ሁኔታው ከዓመት፣ ዓመት ይሻሻላል ብለን ተስፋ ላደረግን ሰዎችም ተስፋችን ተራ ምኞት መሆኑን አስረግጦልን አልፏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሬዲዮ ቀን ሲከበርም ሆነ በሌሎች ጊዜያት ከሚያስተላልፋቸው ተደጋጋሚ መልዕክቶች መካከል የሃሳብ ብዝሃነት ትኩረት እንዲሰጠው የሚያሳስብበት አጀንዳው አንዱ ነው ።የሬዲዮ ቀን ከሚከበርባቸው ዓላማዎች መካከልም አንዱ ሬዲዮ ጣቢያዎች ለሃሳብ ብዝሃነት ትኩረት እንዲሰጡ ለማስገንዘብ ቢሆንም የእኛ አገር ጣቢያዎች መርህና አሠራር ግን ከዚህ በተቃራኒ የቆመ ይመስላል ።

የዓለም የሬዲዮ ቀን እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ ላለፉት 10 ዓመታት ያህል እየተከበረ ዘልቋል ።ለ10 ዓመታት ስለዓለም የሬዲዮ ቀን ያልሰማ የሬዲዮ ጣቢያ ይኖራል ብሎ መገመት በእርግጥም ሹፈት ይመስላል ።

ዘጠኙን ሳያከብሩ 10ኛውንም የደገሙት የሬዲዮ ጣቢያዎች ጉዳይ ነገሩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል ።ቀኑን ለማክበር የሞከሩት ጣቢያዎችም ቢሆኑ ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት እጅግ አነስተኛ ነው ።ይህንን ቀን ለማክበርና ለመዘከር የተለየና የተጋነነ ግብዓትና ወጪ አይፈልግም ።

የዓለም የሬዲዮ ቀንን ማክበርና ለሬዲዮ ውለታዎች እውቅና መስጠት የሬዲዮ ጣቢያዎች ብቻ ሳይሆን የሌሎች መገናኛ ብዙኃን ዘርፎችም (ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ድረ-ገጽ ….) ተግባር መሆን አለበት ።ምክንያቱም ሬዲዮ ለእነዚህ የመገናኛ ብዙኃን ዓይነቶች ማደግ ቀላል የማባል አስተዋፅዖ አበርክቷል ።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጥናት መሠረት ከዓለም አገራት መሪዎች መካከል ከ80 በመቶ የሚበልጡት ሬዲዮ የሚያዳምጡና «ትክክለኛ መረጃ የሚገኘው ከሬዲዮ ነው» ብለው የሚያምኑ ናቸው። በዓለም ላይ ካሉት ጎልማሶች መካከል ደግሞ 70 በመቶዎቹ የሬዲዮ አድማጮች ሲሆኑ፤ ትክክለኛ መረጃ የሚገኘውም ከሬዲዮ እንደሆነ ያምናሉ።

ሬዲዮ ከሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ዓይነቶች ሁሉ በተሻለ ደረጃ ለማህበረሰቡ የላቀ ተደራሽነት አለው ።ለአያያዝም ምቹ ነው፤ በገጠራማ አካባቢዎች ጭምር ተደራሽ መሆን ይችላል፤ አሳታፊ ነው ።

ቀለል ባለ ወጪ ለብዙኃኑ የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ በመሆን ሬዲዮን የሚስተካከል የብሮድካስት ብዙኃን መገናኛ ዘዴ/ዓይነት የለም ።ሬዲዮ መስማት መቻልን እንጂ መማርን (መጻፍንና ማንበብን) አይጠይቅም ።በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ መገናኛ ብዙኃን በበርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተመራጭና ተደማጭ፣ ተዘውታሪ ነው ።

የሬዲዮ ውለታ እንዲህ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም ።በዓለም/በሰው ልጅ የለውጥ ታሪክ ውስጥ ሬዲዮ ያለው አበርክቶ በዋጋ የሚተመን አይደለም ።ይህን የሰው ልጅ ባለውለታ የሆነን ዘርፍ ለሚዘክር ቀን እውቅና አለመስጠት ምን ተብሎ ሊገለፅ እንደሚችል መናገር እጅግ አስቸጋሪ ነው ።ለመሆኑ የሬዲዮ ቀንን የጉዳዩ ዋነኛ ባለቤቶች የሆኑት ሬዲዮ ጣቢያዎች ከዘነጉት/ካላከበሩት ማን ሊያስታውሰውና ሊያከብረው ይችላል?!

ሬዲዮ በተለይ እንደኢትዮጵያ ላሉ አገራት የሚያበረክተው አስተዋፅዖ ዓይነተ ብዙ በመሆኑ የሬዲዮ ቀንን በማክበር ለሬዲዮ ውለታ እውቅና ከመስጠት ባሻገር ዘርፉን ማጠናከር ያስፈልጋል ።ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት በሬዲዮ ከሚተላለፉ መረጃዎችና ከሚፈጠሩ ግንዛቤዎች ውጪ የሚታሰቡ አይደሉም ።

**********************************************************************************************

ምንጭ:- አዲስ ዘመን ጋዜጣ የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

የሬዲዮ ቀን በአለም ለ9ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ


የዓለም የሬድዮ ቀን በኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ  ተከብሯል

የዓለም የሬድዮ ቀን አከባበር በኢትዮጵያ እንዲሁም የሬዲዮ ጋዜጠኞች ገጠመኞች የዘንድሮው የዓለም የሬዲዮ ቀን "ለአዲሱ ዓለም አዲስ አማራጭ" በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ  ተከብሯል።


ማሞ ካቻ (አቶ ማሞ ይንበርብሩ)

  አቶ ማሞ ይንበርብሩ (ማሞ ካቻ) እስቲ እናስታውሳቸው፣ ተቀብሮ እንዳይቀር አኩሪ ታሪካቸው  (ደረጀ መላኩ)   አቶቢሲ ማሞ ካቻ የት ትሄዳለህ? ገብረ ጉራቻ… ታዳጊው ማሞ ይንበርበሩ ገና በጨቅላ እድሜው አባቱ አቶ...