ልጥፎች

እምዬ ያልታደለች

ምስል
  እምዬ ያልታደለች_ በ በረከት በላይነህ   እምዬ ያልታደለች ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች እምዬ ሰከረች ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች! የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋት እያመሱ መዋል — እየፈጩ ማንጋት * * * ይልቅ ግድ የለሽም ! ለቅቤ ጥፍጥና ለቅቤ መአዛ ቅመም ከመደቆስ —ቅመም ከማበጠር ከቅቤያችን በፊት —ከብቶቹን ነው ማንጠር እንስራ ወዝውዞ በጢሳጢስ ናውዞ ለቅቤ ከማማጥ —ለአይብ ከማማጥ ከወተቱ በፊት — እስቲ ላሟ ትናጥ ማለቢያ ከማስፋት —ማለቢያ ከማጥበብ ከግቷ አስቀድሞ ከሆዷ አስቀድሞ —ምግቧን ነው ማጠብ * * * ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ ! * * * ግራ ነኝ ይለኛል ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል? እውቀት አባ አያልቄ እውቀት አባ አይፈሬ —ጥያቄ ሲያድለው ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው * * * እይዉ! ሰው መጠየቅ ትቷል ሰው ፍለጋ ትቷል —ሰው ማጣጣም ትቷል ለመንስኤ ዝሏል —ለአመክንዮ ታክቷል በጥድፊያ ሊያስታግስ —የመሰንበት ሱሱን ጥያቄ ነው ይላል —የከሸፈ መልሱን ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት * * * ኩሬ ነው? ወንዝ ነው? ሃይቅ ነው? ባህር ነው? ጎርፍ ነው? ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ? አዞ አለ? አሳ አለ? . . . እኮ የምን ጥያቄ ! እኮ የምን ክርክር ...

ብዝኃ ጠቢቡ ነቢይ

ምስል
                                         ነቢይ ከጀርመናዊቷ ሪካ ጋር የፈጠረው ግጥማዊ ጥምረት ሔኖክ ያሬድ በዕውቀት አደባባይ ውስጥ ከዚያ ‹የግሪክ ጥበባት›› ከዚህ ‹የግእዝ ጥበባት› የሚባሉ በሰባት መደብ የተከፈሉ የትምህርትና የአዕምሮ ዕድገት መሠረት የሆኑ ትሩፋቶች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ለሥነ ጽሑፍ ከነጓዙ መሠረት የሆነው የቋንቋ ጥናትና አወቃቀሩ (ሰዋስው)፣ በመናገርና በመጻፍ የማሳመን ንግግራዊ ዘይቤ (ሪቶሪክ)፣ የማመዛዘንና የክርክር መርሆችን የያዘው ሎጂክ (ተጥባበ ነገር) ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጥበባት በኢትዮጵያ የትምህርትና የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የተዋሃዱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ትውልዶችም እያበለፀጉ ተጉዘውበታል፡፡ በየዓረፍተ ዘመኑ የሚነሱ ሥነ ጠቢባንም ታይተዋል፡፡ በብዝኃ ጥበባት ካለፉት መካከል ከሰሞኑ ዜና ዕረፍቱ የተሰማው ገጣሚ፣ ጸሐፌ ተውኔት፣ ተርጓሚ፣ ወጋዊ ንግግር አዋቂ፣ ዜናዊ ሆኖ ያለፈው ነቢይ መኰንን ይገኝበታል፡፡ የሥዕል ሥራዎችም አሉት፡፡ ነቢይ፣ ዜናዊ ሲሉት በመጽሔትም (ፈርጥ) ሆነ በጋዜጣ (አዲስ አድማስ) በዋና አዘጋጅነት መሥራቱ ነው፡፡ ‹‹ሰው በዜና ውኃ በደመና›› እንዲሉ ዜናዊ ሆኖ ከሐበሻ ሥነ ልቡና ጋር የተያያዘውን፣ ሠርክ የማይለየውን ተረትና ምሳሌ ከነ ብሂሉ እየዘገነ የርዕሰ አንቀጽ ማንደርደሪያው ማድረጉ ከአገሩ በልዩነት የሚያስቀምጠው ነው፡፡ ‹‹መጽሐፍ ከነገረው ተረት የነገረው›› የሚለውን ነባር ብሂልን ዘመኑ አሻግሮ ያመጣ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የጉዞ ማስታወሻ (ትራቭሉግ) በመጻፍና በማሳተም የሚታወቁት በጣሊያን ያደረጉት...

ብርሃኑ ዘርይሁን የልብወለድ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ጋዜጠኛ

ምስል
  ብርሃኑ ዘርይሁን የልብወለድ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ጋዜጠኛ (Te De) ብርሃኑ ዘርይሁን የልብወለድ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ጋዜጠኛ ነበር።  የድርሰት ሥራዎቹ፦ ► የእንባ ደብዳቤዎች ► ድል ከሞት በኋላ ► አማኑኤል ደርሶ መልስ ► የበደል ፍጻሜ ► ጨረቃ ስትወጣ ► ብር አምባር ሰበረልዎ ► የቴዎድሮስ እንባ ► የታንጉት ምስጢር ► ማዕበል የአብዮት ዋዜማ ► ማዕበል የአብዮት መባቻ እና ► ማዕበል የአብዮት ማግስት ሲሆኑ  ተውኔቶችም፦ ► ጣጠኛው ተዋናይ ► ሞረሽ ► የለውጥ አርበኞች እና ► ባልቻ አባ ነፍሶ ናቸው። በጣም አይናፋር ነው ይሉታል። የሚሰራውን ነገር ላይ በደንብ ጥናት ያደርጋል። የተዋጣለት የታሪካዊ ልብወለድ ደራሲ ነው፦ የታንጉት ሚስጥር፣ የቴዎድሮስ እንባ፣ ማእበል(የአብዮት ዋዜማ፣ የአብዮት መባቻ፣ የአብዮት ማግስት) ምናልባት በኢትዮጵያ ታሪካዊ ልብወለድ ትልቁ ስም ብርሃኑ ዘርይሁን ሳይሆን አይቀርም። ብርሃኑ ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ብዙ መስዋዕትነት ከፍሏል። በጋዜጠኝነት ዘመኑ እውነት እውነት በመፃፉ ከስራ ታግዷል። በመጨረሻ ታላቁን የልብወለድ መጽሐፉን ሳይገላገል አልፏል። በአፄ ቴዎድሮስ ዙሪያ የተፃፉት "የታንጉት" ሚስጥር" እና "አንድ ለናቱ" ሁለቱም ግሩም ታሪካዊ ልብወለዶች ናቸው። ለሁለቱም ደራሲያን ቁንጮ ስራቸው ይመስሉኛል። አቤ ጉበኛ በ"አልወለድም" ልብወለድ መፅሀፉ በግዜውም ሆነ አሁን ድረስ አንገብጋቢ የሆነ ጥያቄ ቢያነሳም ለኔ እንደ ስነፅሁፍ ስራ "አንድ ለናቱ" የሚበልጥ ሆኖ ይሰማኛል። ብርሀኑ ዘርይሁንም "የታንጉት ሚስጥር"ን በፃፈበት ወቅት ችሎታው ጣራ የነካበት ወቅት ይመስለኛል። በመጀመሪያ የተፃፈው "አንድ ለናቱ" በመሆ...

ማሞ ካቻ (አቶ ማሞ ይንበርብሩ)

ምስል
  አቶ ማሞ ይንበርብሩ (ማሞ ካቻ) እስቲ እናስታውሳቸው፣ ተቀብሮ እንዳይቀር አኩሪ ታሪካቸው  (ደረጀ መላኩ)   አቶቢሲ ማሞ ካቻ የት ትሄዳለህ? ገብረ ጉራቻ… ታዳጊው ማሞ ይንበርበሩ ገና በጨቅላ እድሜው አባቱ አቶ ይንበርበሩ በሥራ ምክንያት ወደ ኢሊባቦር ጎሬ ሲዛወሩ አብሮ ሄደ። ብዙም ሳይቆይ አባቱ የጣልያንን ወራሪ ኃይል ለመከላከል ዘምተው፤ በማይጨው ጦርነት የተሰው ሲሆን እናቱ በህመም ምክንያት ቀደም ብለው ሞተው ስለነበር ገና በ12 ዓመት እድሜው ያለ ወላጅ ቀረ። ወላጅ አልባውን ታዳጊ፤ ለግዜው የኢትዮጵያን ሠራዊት አሸንፈው ከገቡት የጣልያን የጦር መኮንኖች አንዱ አግኝቶት ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ይዞት መጣ። ታዳጊው ማሞ አንበርብር አዲስ አበባ በመምጣቱ የዕለት ጉርሱን የማግኘት እድሉ ቀለል አለለት። እዛው አካባቢ የሚገኝን ሻይ ቤት ተጠግቶ ብርጭቆ እያጠበና እየተላላከ በክፍያ መልክ ምግቡን እየሰጡት ኑሮውን ጀመረ። ብልህና ፈጣን ልጅ የነበረው ማሞ አንበርብር በሻይቤቱ ሥራ ብዙም ሳይቆይ፤ በራሱ ሠርቶ ገንዘብ የሚያገኝበትን መንገድ ማሰብ ጀመረ። አስቦም ያገኘው ዘዴ፤ አራት ኩሽኔታ የተገጠመለት መቀመጫ ያለው ተሽከርካሪ ሠርቶ፤ ህጻናትን አሳፍሮ እየጎተተ ከሠይጣን ቤት (ከቴዎድሮስ አደባባይ) እስከ ቴሌኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ድረስ እያንሸራሸረ ገንዘብ ማስከፈል ነበር። ቀስ በቀስ ሳንቲሙ እየተጠራቀመ ሲመጣ አሁንም ሌላ የሕጻናት ማንሸራሸሪያ ተሽከርካሪ አዘጋጀ። ይህ ተሽከርካሪ ሳይክል ሲሆን ፔዳልም ሆነ ካቴና የሌለው አሮጌ ነበር። በሁለቱ ጎማዎች ምትክም ማሞ ራሱ ቆራርጦ የሠራቸው ተሽከርካሪዎች ተገጥመውለት አሁንም እሱን እየጎተተ ሕጻናትን በማንሸራሸር የተሻለ ገንዘብ ማግኘት ጀመረ፡፡   ይህን ማሞን...