ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2015 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አምባሳደር ዘውዴ ረታ ታላቁ የታሪክ ማሕደር ተለየን

ምስል
                                                                 (ከ1927-2008 ዓ.ም) ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከባድ ሃዘን መትቷታል። ታላላቅ ሰዎቿን በሞት ተነጥቃለች።  ባለፈው ሳምንት ደግሞ ታላቁን የታሪክ ፀሐፊ ጋዜጠኛ እና ዲኘሎማት አምባሣደር ዘውዴ ረታ አጥታለች።  ዘውዴ ረታ ብሪታኒያ (ለንደን) ውስጥ አረፉ። ከአንድ ወር በፊት ነሀሴ 7 ቀን 2007 ዓም አምባሣደር ዘውዴ ረታ የተወለዱበት የ80 ዓመት የልደት ቀናቸው ነበር። የማስተር ፊልምና ኮሚኒኬሽንስ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ቢኒያም ከበደ ለኚህ ታላቅ ሰው የሚመጥን ዝግጅት አድርጐ የዘውዴ ረታን የ80 ዓመት የልደት በአላቸውን ጐፋ ገብርኤል በሚገኘው መኖርያ ቤታቸው በደማቅ ሁኔታ አከበረላቸው። እኔም በዚህ የልደት በአላቸው ቀን ተጋብዤ የዘውዴ ረታን የመጨረሻውን የልደት በአል አከበርኩ። ያቺ ቀን ፈጽሞ አትረሣኝም። ምክንያቱም ዘውዴ ረታ ትልቅ ኢትዮጵያዊ የገዘፈ ስብእና ብሎም በሕይወት ያሉ የዘመን ተራኪ ብእረኛ በመሆናቸው ነው። ከእንዲህ አይነት ሰው ጋር ዳቦና ኬክ ቆርሶ መቋደስ፤ የኋላና የፊት የኢትዮጵያን ታሪክ ማውጋት፤ ከቶስ በ...