ልጥፎች

ከጁላይ, 2016 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ንባብ ለሕይወት!

ምስል
http://www.sendeknewspaper.com___በድንበሩ ስዩም___ Thursday, 14 July 2016 ******************************************************************************************************** መጽሐፍት ዓለም ሁሉ የቀየሩ የስልጣኔ ዋና ቁልፎች ናቸው። ዓለም እዚህ የደረሰችው መፃሕፍት ታትመው ነው። የሰው ልጅ የዕውቀት ብልፅግና፣ ልዕልና፣ ሃያልነት፣ ግርማ ሞገሱ ሁሉ ከመፃሕፍት ጋር የተቆራኘ ነው። መፃሕፍት የሌለውና የማያነብ ሰው ባዶ ቤት ውስጥ፣ ምንም ነገር በሌለበት ብቻውን እንደሚኖር ፍጡር ይቆጠራል። የሚያናግረው ሰው እንደሌለው፣ የሚያየው፣ የሚያልመው ሃሳብ እንደሌለው ፍጡር ይቆጠራል። ማንበብ የሰው ልጅ መሆንን ይጠይቃል። ሰው ፣ ሰው ለመሆን ማንበብ አለበት። ካለበለዚያ ብዙ ነገሮችን ከሌሎች እንሰሳት ጋር ይጋራል። የሰው ባህሪያትን ያጣል። የዓለም የሥልጣኔ አውራ ከነበሩት አገራት መካከል አንዷ የነበረችው ሐገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ የሥልጣኔ ውራ ሆናለች። የዚህ ምክንያቱ ሌላ አይደለም። የዕውቀት ማነስ፣ ያለማንበብ ችግር የፈጠረብን አበሳ ነው። ሌላው ዓለም የበለጠን በማንበቡ ነው። ንባብ የሕይወት መሠረት ነው። በጋዜጠኞች በቢኒያም ከበደ እና በአንተነህ ከበደ የሚመራው የዘንድሮው “ንባብ የሕይወት” የተሰኘው ታላቅ የመፃሐፍት አውደ-ርዕይም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያለባትን የማንበብ ችግር ለመቅረፍ የተደረገ ሙከራ ነው። እሰየው ደግ አደረጋችሁ፤ ወደፊትም በርቱ፣ ጠንክሩ ልንላቸው ይገባል። ዕውቀት ላይ የሚሰራን ማንንም ሰው ትውልድ ያመሰግነዋል። የመፃሕፍት አውደ ርዕይ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተ...