በአበሻ አረቄ አከርካሪውን የተመታው ወረርሽኝ!
ከሣህሉ ዓለማየሁ ( ኢንጂነር ) ***************************** እ . ኤ . አ በ 1918 እና 1919 ዓ . ም ስፓኒሽ ፍሉ ( የህዳር በሽታ ) የተባለ ወረርሽኝ በሽታ ዓለምን ባተራመሰበትና 1/3 ኛውን የአውሮፓ ህዝብ በፈጀበት ዘመን፣ በኢትዮጵያም ሰው በተቀመጠበትና በተኛበት ሞቶ በሚቀርበት፣ ሰው ሞቶ ቀባሪ አጥቶ ጅብ የሰው ስጋ አማርጦ መብላት በሰለቸበት በዚያ ክፉ ዘመን፣ ኢትዮጵያዊቷ የባህል መድኃኒት አዋቂ ( የአበሻ ዶክተር ) መንዜዋ ወ / ሮ ዘነበች፣ ወደ አዲስ አበባ ከተማ መጥተው፣ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ፤ “ የአገሬ ህዝብ ሆይ ! ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ በሽታ ለመዳን ከፈለግህ፣ የአበሻ አረቄ ( ካቲካላ ) ጠጣበት፤ ቀይ ሽንኩርት ልጠህ በክር አስረህ፣ በቤት በርና መስኮት ላይ አንጠልጥል ” በማለት አዋጅ አስነገሩ። ይህንን የወ / ሮ ዘነበችን አዋጅ የሰማ የፈረንሳይ ቆንስላ ተደናግጦና ተቆጥቶ፣ “ አረቄ ( አልኮል ) መጠጣት በሽታውን ያባብሳልና አልኮል መጠጣት ክልክል ነው ” እያለ በከተማው ውስጥ በየቦታው እየተዘዋወረ የበኩሉን አዋጅ አስነገረ፡፡ ነገር ግን የፈረንሳዩ ቆንስላ ያስነገረውን አዋጅ የሰማው እንጂ ከቁም ነገር የቆጠረው ኢትዮጵያዊ ባለመኖሩ ማሳሰቢያው ተቀባይነት አጣ፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ የፈረንሳይ ቆንስላውን ( የፈረንጁን ) ምክር ትቶ የአገሩን ተወላጅ የአበሻ ዶክተሯን የወ / ሮ ዘነበችን ምክር ተቀብሎ የታመመው ለመዳን፣ ያልታመመው ደግሞ በበሽታ...