ልጥፎች

ከማርች, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የገጣሚ ነብይ መኮንን እማይነትበዉ ስዉር-ስፌት

ምስል
በ ሀያሲ እና ፀሐፊ አብደላ ዕዝራ **************************  በጥሞና ስለአራት ግጥሞች ፩ ሀገርህ ናት በቃ !  አያሌ ገጣሚያን ሀገር ስትፈካ፣ ሀገር ስትፋቅ፣ ገሃድ ሲገጣጠብ ወይም ሲያብረቀርቅ ግለሰቡ እኔ ምን አገባኝ የመሰለ ገለልተኝነት እንዳይጠናወተዉ ተቀኝተዋል:: ስለ አገር ያልፃፈ የአማርኛ ገጣሚ የለም:: ብዙዎቹ በፍቅር በናፍቆት፣ ጥቂቶቹ እየረገሟት፤ እንደ ወዳጅም እንደ ደመኛም:: ሆድ የባሰዉ፣ ያቄመ፣ ተገፍትሮ ዉስጡ ያመረቀዘ ለሱ <ሀገር> ምኑ ናት ? ያምፅ ይሆናል ወይም ይስለመለማል:: አገር ሲባል ግዑዙ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰቡ፣ ባህሉ፣ ዕምነቱ፣ ወዳጅና ዘመድ ... ይጠራራሉ:: ስብሐት በ <አምስት ስድስት ሰባት> አጭር ልቦለዱ የገለፀዉ በርሱፈቃድ <... ሰሞኑን ስለ ክርስቶስ ስቅለት ትሰማላችሁ:: ግን ማነዉ ሰዉ ሆኖ ያልተሰቀለ? ማነዉ በልጁ ለቅሶ ያልተቸነከረ? ማነዉ በሚስቱ ሞት ያልተቀበረ? ... ከነልጆቹ ረሃብ ሲከታትፈዉ ለሀገርም ለስቅለትም ህሊናዉ ይሻክራል:: እንግዲህ ባለቅኔ የት ሆኖ? ገጠመኙ ምን ቋጥሮ ፃፈ ? የግጥሙ ተናጋሪ personna ንቃተ ህሊናዉ እንደነገሩ ነዉ ወይስ ተመስጧል ? ዘመነኛ ሂስ ፅሑፍን እንጂ የወቅቱን መንፈስና የባለቅኔዉን ግለታሪክ ማሰስ አያደፋፍርም:: ነቢይ ከአማርኛ ገጣሚያን የሚለየዉ አንድ-ሁለት ሳይሆን፣ በአገር ጉዳይ ከሃያ ግጥሞች በላይ መቀኘቱ ነዉ:: የኛ ሰዉ በአሜሪካ መፅሐፍ ልዩ ጣዕሙ ስለ አገር ቤት ትዝታ፣ ኑሮ፣ ህልም ... እያጠለለ ገፆቹ ርሰዉ ስላፈሰሱም ነዉ:: ግለሰብ እትብቱንና ስሩን የተቀማ ተንሳፋፊ እንዳይሆን ይሰጋል:: ሥነቃሉም <አገር አላት ይበሉኝ፣ ማህደረ ማርያም ቅበሩኝ> ሲል...