ጌታቸው ጋዲሳ__ኢትዮጵያ
የናፍቆት ትዝታሽ ካለን በሕይወት፣ ፍፁም የማንረሳሽ ውድ አገር እናት፤ ይኽ ነው አይባልም ክብር ኩራታችን፣ በነፃነት ስንኖር በኢትዮጵያዊነታችን ። 🎵🎵 🎵 ያብሮ አደግ ያብሮ አደግ ጓደኛ... ጓደኛ ትዝታው አይለቀን፣ ሜዳው ሸንተረሩ ሁሌ 'ሚናፍቀን፤ ናፍቆቱ ያደግንበት መንደር ... መንደር መቼ ይረሳና፣ ሌት ተቀን ብንባዝን ማን እንዳንቺ አለና፣ ክፉ አይንካሽ ሁኚ ደህና ክፉ አይንካሽ ሁኚ ደህና። 🎵🎵 🎵 የምሽት የንጋት ነፋሻ አየር፣ ከልብ የሚወደድ የሚፈቀር፤ በአእዋፋት ዝማሬ ታጅቦ፣ ሌሊቱ ነጋ ... ነጋ በፍቅር ታጅቦ፣ ተውቦ። ወግና በዓሉ ያገራችን፣ ያ ውዳመት የሰንበት ኅብረታችን፤ የክረምት የበጋ፣ ባለፀጋ፣ ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ ... ሸጋ። 🎵🎵🎵 ውዲቷ እናት ዓለም ለኛ ... ለኛ ምትክ የሌለሽ፣ ከአይምሮ አይጠፋም ያንቺ ትዝታሽ፤ በፍቅር አየርና ምድርሽ ... ምድርሽ ለሁሉ 'ሚስማማ፣ የደግ ምሳሌ ውብ ዓለም እማማ፤ ምድርሽ ደጉ የሚለማ የደግ ምሳሌ ውብ ዓለም እማማ፤ ምድርሽ ደጉ የሚለማ። 🎵🎵 🎵 ብዙ ውለታን አለሽ በልጆችሽ፣ መኖር እንመርጣለን ሳንለይሽ፤ ፍቅርሽ በልባችን የሚኖር፣ ማንም አይለየን ካንቺ ከሞት በቀር ... በቀር። የአያት የቅድመ አያት ታላቅ ቅርስ፣ ጎራዴ ጋሻቸው ሲታወስ፤ በቅኝ ያልተገዛሽ መሬታችን፣ ነፃነት ነው ክብራችን፣ የጀግንነታችን። ወግና በዓሉ ያገራችን፣ ያውዳመት የሰንበት ኅብረታችን፤ የክረምት የበጋ፣ ባለፀጋ፣ ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ት ዮ ጵ ያ ለምለሚቷ ሸጋ ኢ ት ዮ ጵ ያ ... ኢ ...