«የሬዲዮ ቀን»ን የማያከብሩት ሬዲዮ ጣቢያዎች
በ አንተነህ ቸሬ በየዓመቱ የካቲት 13 (እ.አ.አ) የዓለም የሬዲዮ ቀን (World Radio Day) ተከብሮ ይውላል ።የዓለም የሬዲዮ ቀን ሬዲዮ ለዓለም ያበረከተውንና እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ የማሰብና የሬዲዮን ልዩ ገፅታዎች/ባህርያት የማስገንዘብ ዓላማ አለው ። በዕለቱ ሬዲዮ ከሌሎቹ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎች ስለሚለይባቸውና ተመራጭ ስለሚሆንባቸው ባህርያቱ እንዲሁም ሬዲዮ ለዓለም ሕዝብ ስላበረከታቸው አስተዋፅኦዎችና ስለዋላቸው ውለታዎች በስፋት የሚነገርበትና የሚዘመርበት ነው ።ሬዲዮ ያሉበትን ውስንነቶች ስለማሻሻልና ስላጋጠሙት ችግሮችም ይመከራል ። እ.አ.አ በ2010 የስፔን የሬዲዮ አካዳሚ (Spanish Radio Academy) ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀን (World Radio Day) እንዲሰየም ለአገሪቱ መንግሥት ጥያቄ አቀረበ ።የስፔን መንግሥትም የአካዳሚውን ጥያቄ ተቀብሎ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (UNESCO) አቀረበ ። የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ለተቋሙ ጠቅላላ ጉባዔ ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሠረት የካቲት 13 (እ.አ.አ) የዓለም የራዲዮ ቀን ሆኖ በየዓመቱ እንዲከበር እ.አ.አ በ2011 ውሳኔ አስተላለፈ ።ቀኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሬዲዮ (UN Radio) ከተቋቋመበት ቀን (እ.አ.አ የካቲት 13 ቀን 1946 ዓ.ም) ጋር ይገጣጠማል ። የመጀመሪያው የዓለም የሬዲዮ ቀን የተከበረው እ.አ.አ በ2012 ሲሆን በወቅቱ በእንግሊዝ፣ በስፔን፣ በስዊዘርላንድ፣ በኢጣሊያ፣ በባንግላዴሽና በሌሎች አገራት በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተከብሮ ነበር ።በጊዜው አንዳንድ አገራት የቀኑን አከባበር የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ ልዩ ኮሚቴዎችንም አቋቁመው ነበር ። የተለያዩ አገራት ቀኑን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ያከብሩታል ።በሬዲዮ ጣቢያዎች ከ...