ልጥፎች

ከ2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አማርኛ ቋንቋ ከውጪ ቋንቋዎች የተዋሳቸው ቃላት

  አማርኛ ቋንቋ ከውጪ ቋንቋዎች የተዋሳቸው ቃላት ምሳሌዎች፦ ከግሪክኛ፦ ጠረጴዛ ከአረብኛ፦ ባሩድ ከቱርክኛ፦ ሰንደቅ ከፈረንሳይኛ፦ ባቡር ከጣልኛ፦ ቡሎን ከእንግሊዝኛ፦ ኢንተርናሽናል የሀገራችን ቋንቋዎች ከውጪ ቋንቋዎች በርካታ ቃላትን ወርሰዋል፡፡ ይህም ከብሉይ ዘመን ጀምሮ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡ የመወራረሱ አድማስ ስፋቱን የጨመረው ግን በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቀጣዮቹ አንድ መቶ ሀያ ዓመታት ውስጥ የታዩት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ክስተቶች የሀገራችን ቋንቋዎችን ለውጪ ቋንቋዎች ተጽእኖ የበለጠ ክፍት እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡ ታዲያ ከሶስት ሺህ ከሚልቁት የውጪ ቋንቋዎች መካከል ለሀገራችን ቋንቋዎች ብዙ ቃላትን ለማውረስ የበቁት አራቱ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም  ዐረብኛ፣  ፈረንሳይኛ፣  ጣሊያንኛና  እንግሊዝኛ ናቸው፡፡  የቱርክ እና የጀርመን  ቋንቋዎችም ጥቂት ቃላትን ለሀገራችን ቋንቋዎች አበርክተዋል፡፡ ***** ዐረብኛ በሀገራችን ቋንቋዎች ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር የቻለው በዋናነት የእስልምና ሀይማኖት የአምልኮና የትምህርት ቋንቋ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ከእስልምና እምነት ጋር በተያያዘ ለአምልኮና ለትምህርት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቃላት በአብዛኛው ከዐረብኛ የተገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ መስጊድ/መስጂድ፣ ኢማም፣ ቃዲ፣ አዛን፣ መጅሊስ፣ መድረሳ ወዘተ… የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በሂደት ደግሞ የዐረብኛ ቃላት በአምልኮ ውስጥ ካላቸው አስፈላጊነት አልፈው በተራው ሰው ንግግር ውስጥም ገብተዋል፡፡ ይህ ክስተት በስፋት የሚስተዋለው ግን አብላጫው ነዋሪ ህዝብ ሙስሊም በሆነባቸው እንደ ወሎ፣ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጅማ፣ ሶማሊ (ኦጋዴን)፣ ቤኒሻንጉልና አፋር አካባቢዎች ነው፡...

ያልተዘመረለት ታላቅ ሰዉጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መቆያ

ምስል
  እሸቴ አሰፋ አሳምነው  ESHETE ASSEFA ASAMNEW እሸቴ – ከጃንሜዳ የማይዘነጋ  ዛሬም የሚተጋ  በሳል የሚድያ ሰው እሸቴ አሰፋ  እሸቴ ስለራሱ ከሚናገር ይልቅ ስራው የሚናገር በሳል ባለሙያ ነው፡፡ በመጽሄት ፣ በጋዜጣ፣ በሬድዮ በቲቪ የሰራ ለወጣት ባለሙያዎች አርአያ የሚሆን የተከበረ ባለሙያ ነው፡፡  ትውልድና እድገት እሸቴ አሰፋ የተወለደው ሰሜን ሸዋ መንዝ ግሼ ወረዳ ነው፡፡ ጊዜውም ሀምሌ 19 ፤1953 አ.ም ነበር፡፡ የሚድያ ባለሙያ እሸቴ፣ በተወለደበት እለት፣ታትሞ የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣን፣ አይተን እንደተረዳነው፣ በምእራብና በመካከለኛው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች፣ ቀኑን ሙሉ ደመና ነበር፡፡ በተለይ ጠዋት ሰማዩ በሙሉ ተሸፍኖ አንዳንድ ጊዜ አነስተኛ ዝናብ ከሰአት በኋላ መጠነኛ ዝናብ ይጥል ነበር፡፡ ጋዜጠኛ እሸቴ፣ በተወለደበት እለት ምን ጉዳይ ነበር ብለን፣ ዳሰሳ ስንሰራ፣ አዲስ ዘመን ባወጣው የፊት ለፊት ገጽ ዜና፣ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ያላት ተቀማጭ ገንዘብ፣ከ15 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ያለ ነበር፡፡ የስራ አመራር ኮርስም የተቋቋመው የዛኑ ሰሞን ነበር፡፡ የጋዜጠኝነት ጅማሮ -በወጣትነት እሸቴ አሰፋ፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበትና ባደገበት፣ ግሼ ወረዳ በሚገኘው ራቤል ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ 2ኛ ደረጃን፣ በ መሃል ሜዳ፣ በሆለታና አቃቂ ተማሪ ቤቶች ነበር ተምሮ ያጠናቀቀው፡፡፡፡ የእሸቴ የሚድያ እና የጋዜጠኝነት አፍቃሪነት የታየው፣ ገና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ ነበር፡፡ ያንጊዜ በተማሪ ቤቱ ሚኒ ሚድያ፣ በጥዋቱ የተማሪዎች ሰልፍ ላይ የስነ-ጽሁፍ ስራዎችን በማቅረብ እጅና አንደበቱን አፍታታ፡፡ እሸቴ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ጽሁፍ የታተመለት ፣ በአዲ...

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ እያዋዛ የሚያስተምረው ርዕሰ አንቀፅ

ምስል
አዲስ አድማስ   በ ኢትዮጵያ   ዘወትር ቅዳሜ የሚታተም   ሳምንታዊ   ጋዜጣ   ነው። ጋዜጣው የሚታተው በአድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ . የተ . የግ . ማ . ሲሆን የተመሰረተው በ ታኅሣሥ ፳፱   ቀን   ፲፱፻፺፪   ዓ . ም . ነው።   ( አዲስ አድማስ ታህሳስ 29 ቀን 1992 ዓ . ም የመጀመሪያው ዕለተ ቅዳሜ ለንባብ በቃ !! ) በአሁኑ ጊዜ የጋዜጣው ሥራ አስኪያጅ ገነት ጎሳዬ ስትሆን ዋና አዘጋጅ ደግሞ ነቢይ መኮንን ነው። ################################################################################ ቅዳሜ  መ ስ ኮ ረ ም  28  ቀን  2015  ዓ . ም  Saturday, 08 October 2022  “አሁን ለምንድነው ፈሪ ማቀንቀኑ ቅጠል አይበጠስ ካልደረሰ ቀኑ!” ከዕለታት አንድ ቀን ልክ እንደ ደራሲ ስብሐት ልብ ወለድ ባሕሪ፤ እንደ አጋፋሪ እንደሻው፤ ሞትን የሚፈሩና የሚሸሹ አቶ መርኔ የሚባሉ ባላባት ነበሩ፡፡ የሰፈሩ ሰው አብዬ መርኔ እያለ ነው የሚጠራቸው፡፡ አቶ መርኔ ሞትን ለማሸነፍ ሲሉ ወደፊት የሚሆነውን ነገር የሚተነብዩ ኮከብ ቆጣሪዎች ዘንድ ሄደው ያውቃሉ፡፡ ኮከባቸውን አስቆጥረዋል፡፡ የወደፊታቸው ሁኔታ፣ ፍፃሜያቸው ምን እንደሚሆን ለማወቅ ከጅለው፡፡ የመዳፍን መስመር እያዩ የሰውን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚናገሩ መዳፍ አንባቢዎች ዘንድም ሄደዋል፡፡ ዕጣዬን እዩልኝ ብለው የተለያዩ አዋቂዎችን  ጠይቀው አስነብበዋል። ሞራ ገላጮች የሚባሉ የሰው መፃዒ ዕድል ተናጋሪዎችም ጋ ሄደው የወደፊት ፍፃሜ ሕይወታቸውን ለማረ...