ጌትሽ ማሞ _ወደ ኋላ _2014/2022
ጌትሽ ማሞ _ወደ ኋላ 💚💛❤️ እስኪ ሰላም ብዬ ነገር ልጀምር፣ አዬ መቸስ እንደችግር የለም የሚቸግር፣ ዝም አልልም እኔ እሳት ይዞ መቶ እያቃጠለኝ፣ አዬ ሰላም ነው ይለኛል ሰላም ሳይሰጠኝ። ዝም አልልም እኔ በቃ ዝም አልልም ድምፄ ቢኮስስም ባይሰማችሁ፣ አዬ ከእውነቱ መንገድ እስካልቆማችሁ፣ ዝም አልልም እኔ ሞት እንኳ ቢምጣ ቢቆም ከበሬ፣ አዬ ፍትህ እጠይቃለሁ ዝም አልልም እኔ። ዝም አልልም እኔ ዝም አልልም እኔ ዝም አልልም በቃ ዝም አልልም ሜዳ ወንዛወንዙ ጋራው ሸንተረሩ ያገሬ አፈር፣ ከእምዬ ጓዳ ያጣነው ሳይኖር፣ መግባባት አቅቶን ወርሶን ድህነት፣ መለያችን ሆነ እራብ ጦርነት። በዚህ ሲሉት በዚያ በዚያ ሲሉት በዚህ ሆኖ ነገራችን፣ ስጋት እየሆንን አንዳችን ለአንዳችን፣ ለክፍም ለደጉም ትወጣለች ፀሃይ፣ አልቃሽም አስለቃሽ ይውላል አንድላይ። ሁላችንም ፈራጅ ሁላችንም ወቃሽ፣ ሁላችንም አዝማች ሁላችንም አልቃሽ፣ አድረን እያነስን ጊዜው ቢለን ሌላ፣ ከፊት የነበርነው ቀረን ወደኋላ። ወደኋላ ወደኋላ ወደኋላ ወደኋላ ቀረን ወደኋላ ወደኋላ ወደኋላ ወደኋላ እንዲያው ስንባላ እራስ አርጎ ፈጥሮን ሆነን ቀረን ጭራ እንዲሁ ስንባላ ወደኋላ ድምፄ ቢኮስስም ባይሰማችሁ፣ ከእውነቱ መንገድ እስካልቆማችሁ፣ ሞት እንኳ ቢምጣ ቢቆም ከበሬ፣ ፍትህ እጠይቃለሁ ዝም አልልም እኔ። ዝም አልልም እኔ በቃ ዝም አልልም የሚያቀራርበን ሃሳብ ይዞ መጥቶ ከፊት የሚያቆመን እንዴት እንቸገር አንድ ሰው አጥተን። እ ብሎ ከአንጀቱ ቆሞ እንደማረከሽ ሰው አይውጣልሽ ብሎ ማነው የረገመሽ ቀኝ አውለኝ ብሎ ሰው ማልዶ ተነስቶ ሲወጣ ከቤቱ መች በሌላ ሆነ ...