የኢትዮጵያ ኮከብ
በ- አብነት ስሜ
የመጽሐፉ ዋና መከራከሪያ ዘመን በየሁለት ሺህ ዓመቱ ይለወጣል፤ በሦስተኛው
ሚሌኒየም የአኳሪየስ ዘመን ገብቷል፤ የኢትዮጵያ ኮከብ አኳሪየስ ነው፤ የአኳሪየስ ዘመን አኳሪየስ ለሆነችው ኢትዮጵያ ከጉዳቱ ይልቅ
ጥቅሙ ያመዝናል፤ የሚል ነው፡፡ ትንታኔው የተካሔደው በአስትሮሎጂ ማዕቀፍ ውስጥ ነው።
መጽሐፉ በአምስት ክፍልና በአስራ ሰባት ምዕራፎች ተደራጅቶ ቀርቧል። ለትንታኔው
ዳራ ለመስጠት ሲባል የአስትሮሎጂ ታሪካዊ አመጣጥና አሠራር በክፍል አንድ ተመጥኖ ቀርቧል። በዚህ ክፍል ስለዋና ኮከብና ስለ ልደት
ሰንጠረዥም አጭር ማብራሪያ አለ። በዚህ ክፍል ባለው የመጨረሻ ምዕራፍም የዘመናት ኮከብ ምጥን ገለፃ ይገኛል። የክፍል ሁለት ዋና
ትኩረት 8ኛው ሺህ ስለሚባለው ስለ አኳሪየስ ዘመን ነው። በዚህ ክፍል የአኳሪየስ ዘመን ባህሪ ከአኳሪየስ ኮከብ ፀባይ ተፅእኖ እና
ከሊዮ ኮከብ ንኡስ ተፅእኖ አንፃር ተብራርቷል። ክፍል ሦስት ወደ ኋላ መለስ ይልና የአስትሮሎጂን ጥቅሞች እና ምክሮች ያቀርባል።
ምክሮቹ በተለይ በጤናና በሙያ ዝንባሌ ላይ ያተኩራሉ።
ክፍል አራት በሀገራት ኮከብ መጠነኛ ገለፃ ይንደረደርና የኢትዮጵያ ኮከብ
ላይ ሙሉ ትኩረቱን ያደርጋል። ክፍል ሁለትና ክፍል አራት የመጽሐፉ ማእከላዊ ይዘቶች ናቸው። በክፍል አምስት ሦስት አባሪዎች ተካተዋል።
አባሪ 1 ስለ ጉዱ ካሳ ኮከብ በ2001 የተፃፈ ብእሮግ ነው፡፡ አባሪ 2፣ በ1999 ስለ ኢትዮጵያ ኮከብ የጻፍኩት አጭር ብእሮግ
ነው። አባሪ 3፣ የውጭ አገርና የኢትዮጵያውያን ስመጥር ግለሰቦችን ኮከብ አጭር ዝርዝር ይዟል። በዚህ አባሪ፣ የሀገራትና የገፀባህርያት
ኮከቦች ዝርዝርም ይገኛል።
**************************************
ምንጭ:--http://semnaworeq.blogspot.com/
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ