ጀግናው በላይ ዘለቀ
ጀ ግናው በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ / ሮ ጣይቱ አስኔ በወሎ ክፍለ ሐገር በቦረና ሳይንት አውራጃ በጫቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ በ 1904 ዓ . ም ተወለዱ። በተወለዱ በአራት ዓመታቸው አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ እያሱ ባለሟል ሆነው የአንድ ክፍለ ጦር ኃላፊ ስለነበሩ ልጅ እያሱ በተያዙ ጊዜ ከዚያ አምልጠው በቦረና ሳይንት አውራጃ በጨቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጣቀት መድሉ ከተባለው ቀበሌ ተቀምጠው እንዳሉ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በፀብ መካከል የሰው ህይወት ያልፍባቸዋል። ለዚህም ምክንያት ወሎን ለቀው ወደ ጐጃም መጡ። ጐጃምም በተለይ በቢቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ ልዩ ስሙ ለምጨን ከተባለው ቀበሌ ተቀመጡ። ብቸና ውስጥም ተቀምጠው ሳለ እርሳቸውን የሚያስስ ልዩ ጦር በጥቆማ ወደ አካባቢው ተላከ። ከዚህ ጦር ጋርም ከፍተኛ ውጊያ ተደረገ። በዚህ ውጊያ ወቅት በላይ ዘለቀ እና እጅጉ ዘለቀ ልጆች ቢሆኑም ተኩሱን እያዩ የሚወድቁትን ጥይቶች ይቆጥሩ ነበር። ከውጊያው በኋላም የበላይ ዘለቀ አባት ተመተው ይወድቃሉ። ይሞታሉ። እነ በላይ ዘለቀም ካለ አባት ከእናታቸው ከወ / ሮ ጣይቱ አሰኔ ጋር ማደግ ይጀምራሉ። ከፍ ሲሉም የአባታቸውን ገዳይ እና አስጠቁሞ እየመራ ያስገደላቸው ማን እንደሆነም ለማወቅ ማሰስ ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ፋሺስት ኢጣሊያ በ 1928 ዓ . ም ኢትዮጵያን ወረረች። በላይ ...