ያወጣሁ ያወረድኩት ሀሳብ
Chasing Beautiful Questions እንዲህ አሰብኩ ። ሜኒያፖሊስ አየር መንገድ የአይሮፕላኑ መንደርደሪያ መስክ ላይ እኔን እና ብዙ ፈረንጆችን የተሳፈርንበት የብረት አሞራ ወደ ሰማይ ለመምጠቅ ሲንደረደር አንድ ሀሳብ ወደ አእምሮዮ መጣ።እሳቤውን የጫረልኝ አንድ እግሩን በቀን ጎዶሎ ያጣ ፈረንጅ ነው። ገና የ 21 ዓመት ጐረምሳ ሳለ በበጋው ወራት አሪዞና ውቅያኖስ ዳርቻ ፈረንጆቹ ዋተር እስኪንግ የሚሉትን በእኛ አገር እይታ ቅብጠት በእነሱ ደግም እስፓርት ጨዋታ ላይ እንዳለ ያልታሰበ የሞተር ጀልባ ገጭቶት እራሱን ይስታል ። እራሱን ያወቀው እሆስፒታል ውስጥ ነበረ ። መመልከት አልፈልግም ግን ልመልከተው አለ ግራ እግሩ ተቆርጧል እጂግ ልብን የሚሰብር ሀዘን ነበር። የሆስፒታሉ ፕሮስቴቲክ ወይም የሰው ሰራሽ እግር ሞያተኞች በአሉሚኒየም የተሠራ እግር አመጡለት እናም ከብዙ ማስጠንቀቂታያ ጋር ከሆስፒታል ወጣ። ለመጀመርያ ጊዜ በአዲሱ ሰው ሠራሽ እግር ለመራመድ ሲውተረተር እንደ ጐማ ተጠቅልሎ ነበር የወደቀው ።ከዚያች ሰከንድ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አይነት ቅብጠት እንደማያዋጣ ገባው ።ዶክተሮቹ በቀን ሁለት ጊዜ ያውም ብዙ ነገር እየተደገፈ እዲሞክር ቢያዙትም እርሱ አሻፈረኝ ብሎ ከደንቡ ውጪ ልራመድ ሲል ነው ዋጋውን ያገኘው። ፊሊፕ የተባለው ይህ ጀብደኛ ጕረምሳ ጭራሹኑ የእግሩን መቆረጥ አላምንም ማለቱ ነበር በጊዜው ብዙውችን ግራ ያጋባው ።የእጮኛው አባት አይዞህ ፊሊፕዬ እስክትለምደው ድረስ ነው ከትንሽ ጊዜ በኋላ ትቀበለዋለህ አለው።እርሱ ግን የእግሩን አለመኖር ማመን አልቻለም ።ከንፈሬን በንዴት ነከስኩት ይላል ፊሊፕ ።እውነቱን ነው ማንም ሰው በሚረዳበት አረዳድ ከወሰድነው እግሬ ተቆርጧል ብዬ ከማመን ውጪ አማራጭ የለኝም ግን...