ልጥፎች

ከማርች, 2015 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አዛዥ ሐኪም ወርቅነሕ እሸቴ(ዶ/ር ማርቲን)!!

(በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሐኪም) ************************************** በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል በኖረው ታሪክ መቸም ቢሆን በማይዘነጋው የመቅደላው ግብግብ በወራሪው ወታደሮች ሳይቀር በሚገባ የተወደሰው የመይሳውን የክብር አሟሟት ባስገኘልን ልዕልና ፋንታ ከዚሕ አስደናቂ ታሪክ ጀርባ በደንብ ያልተነገሩ ብዙ እውነቶች በመኖራቸው አቅም በፈቀደ ታሪካችንን ከያለበት እያሳደድን ማቅረባችንን ስንቀጥል ክብር ይሰማናል….በዚሕ የአጭር አጭር ወግ ሁልጊዜም ቢሆን በቁጭት ከሚያንገበግበን የልዑል ዓለማየሁ ስደትና ሞት ጋር የሚዛመድ የአንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ግለ ታሪክ በወፍ በረር ልንቃኝ እድል ቀናን………..በአጼ ቴዎድሮስ የመጨሻዎቹ የሥልጣን ዓመታት በውስጥ ፖለቲካ ምክንያት በመቅደላ አምባ ለእስር የሚጋዙ በርካቶች ነበሩ….ከእነዚሕም መካከል የዛሬው ባለታሪካችን እናትና አባት ነጋድራስ እሸቴና ወ/ሮ ደስታ ወልደማርያም ይገኙበታል…..በ1857 ዓ/ም በጎንደር ከተማ የተወለዱት ወርቅነሕ ገና የሦስት ዓመት ጨቅላ ሳሉ ከወላጆቻቸው ጋር በመቅደላ አምባ ለእስር መደረጋቸው ምን አልባትም የወደፊቱን እጣ ፈንታቸውን ያደላደለ አጋጣሚ መፍጠሩ አልቀረም……በ1860 ዓ/ም የእንግሊዝ ጦር መቅደላን ሲይዝ በተፈጠረው እረብሻ የሞተው ሞቶ የተቀረው እግሬ አውጪኝ ሲል ከተገኙት ሕጻናት መካከል የአጼ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል ዓለማየሁና ሕጻን ወርቅነሕ በእንግሊዝ ወታደሮች ተማርከው ከወራሪው ጦር ጋር ጉዞ ጀመሩ………ከባሕር ወደብ ሲደርሱ ልኡል ዓለማየሁና ሕጻን ወርቅነሕ ሊለያዩ ግድ ሆነ....... ሮበርት ናፔር ልዑል ዓለማየሁን ይዞ ወደ እንግሊዝ ሲያቀና ሕጻን ወርቅነህ ግን ከኮሌኔል ቻርለስ ቻምበርሊን ጋር በመሆን በወቅቱ በእንግሊዝ ቅኝ ግ...