ያልተዘመረለት ታላቅ ሰዉጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መቆያ
እሸቴ አሰፋ አሳምነው ESHETE ASSEFA ASAMNEW እሸቴ – ከጃንሜዳ የማይዘነጋ ዛሬም የሚተጋ በሳል የሚድያ ሰው እሸቴ አሰፋ እሸቴ ስለራሱ ከሚናገር ይልቅ ስራው የሚናገር በሳል ባለሙያ ነው፡፡ በመጽሄት ፣ በጋዜጣ፣ በሬድዮ በቲቪ የሰራ ለወጣት ባለሙያዎች አርአያ የሚሆን የተከበረ ባለሙያ ነው፡፡ ትውልድና እድገት እሸቴ አሰፋ የተወለደው ሰሜን ሸዋ መንዝ ግሼ ወረዳ ነው፡፡ ጊዜውም ሀምሌ 19 ፤1953 አ.ም ነበር፡፡ የሚድያ ባለሙያ እሸቴ፣ በተወለደበት እለት፣ታትሞ የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣን፣ አይተን እንደተረዳነው፣ በምእራብና በመካከለኛው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች፣ ቀኑን ሙሉ ደመና ነበር፡፡ በተለይ ጠዋት ሰማዩ በሙሉ ተሸፍኖ አንዳንድ ጊዜ አነስተኛ ዝናብ ከሰአት በኋላ መጠነኛ ዝናብ ይጥል ነበር፡፡ ጋዜጠኛ እሸቴ፣ በተወለደበት እለት ምን ጉዳይ ነበር ብለን፣ ዳሰሳ ስንሰራ፣ አዲስ ዘመን ባወጣው የፊት ለፊት ገጽ ዜና፣ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ያላት ተቀማጭ ገንዘብ፣ከ15 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ያለ ነበር፡፡ የስራ አመራር ኮርስም የተቋቋመው የዛኑ ሰሞን ነበር፡፡ የጋዜጠኝነት ጅማሮ -በወጣትነት እሸቴ አሰፋ፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበትና ባደገበት፣ ግሼ ወረዳ በሚገኘው ራቤል ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ 2ኛ ደረጃን፣ በ መሃል ሜዳ፣ በሆለታና አቃቂ ተማሪ ቤቶች ነበር ተምሮ ያጠናቀቀው፡፡፡፡ የእሸቴ የሚድያ እና የጋዜጠኝነት አፍቃሪነት የታየው፣ ገና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ ነበር፡፡ ያንጊዜ በተማሪ ቤቱ ሚኒ ሚድያ፣ በጥዋቱ የተማሪዎች ሰልፍ ላይ የስነ-ጽሁፍ ስራዎችን በማቅረብ እጅና አንደበቱን አፍታታ፡፡ እሸቴ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ጽሁፍ የታተመለት ፣ በአዲ...