ልጥፎች

ከጁላይ, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እምዬ ያልታደለች

ምስል
  እምዬ ያልታደለች_ በ በረከት በላይነህ   እምዬ ያልታደለች ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች እምዬ ሰከረች ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች! የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋት እያመሱ መዋል — እየፈጩ ማንጋት * * * ይልቅ ግድ የለሽም ! ለቅቤ ጥፍጥና ለቅቤ መአዛ ቅመም ከመደቆስ —ቅመም ከማበጠር ከቅቤያችን በፊት —ከብቶቹን ነው ማንጠር እንስራ ወዝውዞ በጢሳጢስ ናውዞ ለቅቤ ከማማጥ —ለአይብ ከማማጥ ከወተቱ በፊት — እስቲ ላሟ ትናጥ ማለቢያ ከማስፋት —ማለቢያ ከማጥበብ ከግቷ አስቀድሞ ከሆዷ አስቀድሞ —ምግቧን ነው ማጠብ * * * ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ ! * * * ግራ ነኝ ይለኛል ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል? እውቀት አባ አያልቄ እውቀት አባ አይፈሬ —ጥያቄ ሲያድለው ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው * * * እይዉ! ሰው መጠየቅ ትቷል ሰው ፍለጋ ትቷል —ሰው ማጣጣም ትቷል ለመንስኤ ዝሏል —ለአመክንዮ ታክቷል በጥድፊያ ሊያስታግስ —የመሰንበት ሱሱን ጥያቄ ነው ይላል —የከሸፈ መልሱን ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት * * * ኩሬ ነው? ወንዝ ነው? ሃይቅ ነው? ባህር ነው? ጎርፍ ነው? ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ? አዞ አለ? አሳ አለ? . . . እኮ የምን ጥያቄ ! እኮ የምን ክርክር ...