ከፊልም መንደር
“የኢትዮጵያን ፊልም እንደ ዥዋዥዌ ነው የማየው” 14 December, 2013 Written by አበባየሁ ገበያው *********************** “አሪፍ ሃያሲ ፊት ለፊት እየሄደ መንገድን ያሳያል፣ ቀሽም ሃያሲ ኋላ ኋላ እየተከተለ ይገፋል” አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ አብዛኞቹ የፊልም አድናቂዎች ከ‹‹ሄርሜላ›› ፊልም ጀምሮ ያውቁታል፡፡ በፊልም ትወና ሙያ ለ11 ዓመታት የሰራው አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ፤ በየጊዜው በርካታ የፊልም ፅሁፎች ቢቀርቡለትም እስካሁን በዓመት ከአንድ በላይ ፊልም አልሰራም፡፡ መስራት ሳይፈልግ ቀርቶ አይደለም፡፡ የሚመጥነው እያጣ መሆኑን አርቲስቱ ይናገራል። ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ‹‹የዓመቱ ምርጥ የወንድ የፊልም ተዋናይ›› በሚል የተሸለመው አርቲስቱ፤ የዛሬ ሶስት ዓመትም በተመሳሳይ ዘርፍ ተሸላሚ ነበር፡፡ የ‹‹ሜተድ አክቲንግ›› የትወና ዘይቤ ገፀ ባህርይው መስሎ ሳይሆን ሆኖ መጫወት እንደሚፈልግ ያስረዳል፡፡ ለዚህ ነው የሚተውነውን ገፀ ባህሪ ለማጥናት ሰፊ ጊዜ የሚወስደው፡፡ ዘንድሮ በተሸለመበት በ‹‹400 ፍቅር›› ፊልም ላይ ቦክሰኛውን ሆኖ ለመጫዎት ለስምንት ወር የቦክስ ስልጠና እንደወሰደ ይናገራል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ከግሩም ኤርሚያስ ጋር ባደረገችው ቆይቶ ስለ ህይወቱና ስለ ሙያው፣ ስለ ኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪና ተያያዥ ጉዳዮች አነጋግራዋለች፡፡ በቅርቡ ሁለተኛ ልጅ አግኝተሃል፡፡ ባለፈው ሳምንት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል “የዓመቱ ምርጥ የፊልም ተዋናይ...