ልጥፎች

ከ2014 ልጥፎች በማሳየት ላይ

“ኦሮማይ” እና በዓሉ ግርማ

ምስል
ጸሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ ******************  ኦሮማይ ከልቡ መጽሐፍ ነው፡፡ በአማርኛ ልብ-ወለድ መጻሕፍት (Novel) ታሪክ በጣም አነጋጋሪውና አከራካሪው መጽሐፍ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ፍቅር ካልተነፈጋቸው ጥቂት መጻሕፍት አንዱም ነው፡፡ በህይወቴ ብዙ ጊዜ እየደጋገምኩ ካነበብኳቸው መጻሕፍት መካከልም በመጀመሪያው ረድፍ ይሰለፋል፡፡ ይሁንና ሰዎች ለዚህ መጽሐፍ ያላቸው አድናቆት እንደየ አመለካከታቸው ይለያያል፡፡ መጽሐፉ የብዙዎቹን አትኩሮት የሳበው ታሪኩ እውነት ነው ስለተባለ እና በመጽሐፉ ሳቢያም የደራሲው ህይወት ለአደጋ በመጋለጡ ይመስለኛል፡፡ ከመጽሐፉ ዐቢይ ገጸ-ባህሪያት አንዱ የሆኑት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ “የደም እምባ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ተመሳሳይ እይታ አንጸባርቀዋል፤ እንደ ሻለቃ ዳዊት አባባል ኦሮማይ ባይታገድ ኖሮ ተወዳጅነቱ ይሄን ያህል አይገዝፍ ነበር፡፡ ሆኖም እኔ በዚህ አባባል አልስማማም፡፡ ደራሲው ባይሞት እና ታሪኩ እውነተኛ ባይሆን እንኳ “ኦሮማይ” ተደናቂ የመሆንን እድል አያጣም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህም በርካታ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ “ኦሮማይ” በቅድሚያ ቀልብን የሚስበው በአጻጻፍ ብሂሉ ነው፡፡ ደራሲው ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አጫጭር ዐረፍተ ነገሮችን ይጠቀማል፡፡ ይህም አንባቢው የመጽሐፉን የትረካ ቅደም ተከተል ሳይስት ድርሰቱን ያለድካም እንዲያጣጥም ያግዘዋል፡፡ ደራሲው ጠጣር ሃሳቦችን በቀላሉ ይዘረዝራል፡፡ የዘመኑ መንግሥት አሰራርን ለተደራሲው በሚገባው ቋንቋ ቀለል አድርጎ ያስረዳዋል፡፡ በሌላ በኩል መጽሐፉ ኪናዊ ውበቱን እንዳይስት ደራሲው በእጅጉ ተጠቧል፡፡ ዘይቤአዊ አባባሎችን ከዘመኑ የአነጋገር ፋሽን ጋር እየቀላቀለ አንባቢውን ያዝናናዋል፡፡ በ...

ደራሲ አዳም ረታ

ምስል
  አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው አጫጭር ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት። ከተደራሲው ጋር የተዋወቀበት እና በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ተከታታዮችና አንባቢዎች ልብ ውስጥ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበት “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተ መው በ1977 ዓ.ም ነው። (በዚህ መድብል ውስጥ አራት ስራዎችን አዋጥቷል፡ “ድብድብ” ፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”) ሜጋ አሳታሚ ድርጅት በ1990 ዓ.ም ባሳተመው “ጭጋግና ጠል” የአጭር ታሪኮች ስብስብ “ዘላን” የተባለው ልቦለዱ ታትሟል። እነዚህ ሁለቱ ከሌሎች ደራሲዎች ስራዎች ጋር የታተሙለት ስለሆነ እንደ ወጥ ሳይቆጠሩ ነው ከላይ የሰፈረው የተባለው። በ1981 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ የታተመው “ማህሌት” የደራሲው የመጀመሪያ ወጥ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መፅሀፍ ነው። በሻማ ቡክስ በ1997 ዓ.ም የታተመው “ግራጫ ቃጭሎች” እንደ ብሉይ (classic) ሥራ ሊታይ የሚችልና የደራሲው ልዩ ብቃት የታየበት ወጥ ረጅም ልብወለድ ነው። በ2001 ዓ.ም ሁለት ልዩ ስራዎች ይዞ የቀረበው አዳም፡ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “አለንጋና ምስር” እና እርስ በርሳቸው በቀጭን የታሪክ ክር የሚገናኙ ልብወለዶች (ኖቬላዎች) ያካተተው “እቴሜቴ የሎሚ ሽታ” ለአንባቢያን አበርክቷል። በቀጠሉት ሦስት ዓመታት በየዓመቱ አንዳንድ መፅሐፍ ለአንባቢያ ያደረሰ ሲሆን በ2...

ያወጣሁ ያወረድኩት ሀሳብ

ምስል
Chasing Beautiful Questions  እንዲህ አሰብኩ ። ሜኒያፖሊስ አየር መንገድ የአይሮፕላኑ መንደርደሪያ መስክ ላይ እኔን እና ብዙ ፈረንጆችን የተሳፈርንበት የብረት አሞራ ወደ ሰማይ ለመምጠቅ ሲንደረደር አንድ ሀሳብ ወደ አእምሮዮ መጣ።እሳቤውን የጫረልኝ አንድ እግሩን በቀን ጎዶሎ ያጣ ፈረንጅ ነው። ገና የ 21 ዓመት ጐረምሳ ሳለ በበጋው ወራት አሪዞና ውቅያኖስ ዳርቻ ፈረንጆቹ ዋተር እስኪንግ የሚሉትን በእኛ አገር እይታ ቅብጠት በእነሱ ደግም እስፓርት ጨዋታ ላይ እንዳለ ያልታሰበ የሞተር ጀልባ ገጭቶት እራሱን ይስታል ። እራሱን ያወቀው እሆስፒታል ውስጥ ነበረ ። መመልከት አልፈልግም ግን ልመልከተው አለ ግራ እግሩ ተቆርጧል እጂግ ልብን የሚሰብር ሀዘን ነበር። የሆስፒታሉ ፕሮስቴቲክ ወይም የሰው ሰራሽ እግር ሞያተኞች በአሉሚኒየም የተሠራ እግር አመጡለት እናም ከብዙ ማስጠንቀቂታያ ጋር ከሆስፒታል ወጣ። ለመጀመርያ ጊዜ በአዲሱ ሰው ሠራሽ እግር ለመራመድ ሲውተረተር እንደ ጐማ ተጠቅልሎ ነበር የወደቀው ።ከዚያች ሰከንድ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አይነት ቅብጠት እንደማያዋጣ ገባው ።ዶክተሮቹ በቀን ሁለት ጊዜ ያውም ብዙ ነገር እየተደገፈ እዲሞክር ቢያዙትም እርሱ አሻፈረኝ ብሎ ከደንቡ ውጪ ልራመድ ሲል ነው ዋጋውን ያገኘው። ፊሊፕ የተባለው ይህ ጀብደኛ ጕረምሳ ጭራሹኑ የእግሩን መቆረጥ አላምንም ማለቱ ነበር በጊዜው ብዙውችን ግራ ያጋባው ።የእጮኛው አባት አይዞህ ፊሊፕዬ እስክትለምደው ድረስ ነው ከትንሽ ጊዜ በኋላ ትቀበለዋለህ አለው።እርሱ ግን የእግሩን አለመኖር ማመን አልቻለም ።ከንፈሬን በንዴት ነከስኩት ይላል ፊሊፕ ።እውነቱን ነው ማንም ሰው በሚረዳበት አረዳድ ከወሰድነው እግሬ ተቆርጧል ብዬ ከማመን ውጪ አማራጭ የለኝም ግን...

ጀግናው በላይ ዘለቀ

ምስል
  ጀ ግናው በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ / ሮ ጣይቱ አስኔ በወሎ ክፍለ ሐገር በቦረና ሳይንት አውራጃ በጫቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ በ 1904 ዓ . ም ተወለዱ። በተወለዱ በአራት ዓመታቸው አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ እያሱ ባለሟል ሆነው የአንድ ክፍለ ጦር ኃላፊ ስለነበሩ ልጅ እያሱ በተያዙ ጊዜ ከዚያ አምልጠው በቦረና ሳይንት አውራጃ በጨቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጣቀት መድሉ ከተባለው ቀበሌ ተቀምጠው እንዳሉ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በፀብ መካከል የሰው ህይወት ያልፍባቸዋል። ለዚህም ምክንያት ወሎን ለቀው ወደ ጐጃም መጡ። ጐጃምም በተለይ በቢቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ ልዩ ስሙ ለምጨን ከተባለው ቀበሌ ተቀመጡ። ብቸና ውስጥም ተቀምጠው ሳለ እርሳቸውን የሚያስስ ልዩ ጦር በጥቆማ ወደ አካባቢው ተላከ። ከዚህ ጦር ጋርም ከፍተኛ ውጊያ ተደረገ። በዚህ ውጊያ ወቅት በላይ ዘለቀ እና እጅጉ ዘለቀ ልጆች ቢሆኑም ተኩሱን እያዩ የሚወድቁትን ጥይቶች ይቆጥሩ ነበር። ከውጊያው በኋላም የበላይ ዘለቀ አባት ተመተው ይወድቃሉ። ይሞታሉ። እነ በላይ ዘለቀም ካለ አባት ከእናታቸው ከወ / ሮ ጣይቱ አሰኔ ጋር ማደግ ይጀምራሉ። ከፍ ሲሉም የአባታቸውን ገዳይ እና አስጠቁሞ እየመራ ያስገደላቸው ማን እንደሆነም ለማወቅ ማሰስ ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ፋሺስት ኢጣሊያ በ 1928 ዓ . ም ኢትዮጵያን ወረረች። በላይ ...