ብርሃኑ ዘርይሁን የልብወለድ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ጋዜጠኛ
ብርሃኑ ዘርይሁን
የልብወለድ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ጋዜጠኛ (Te De)
ብርሃኑ ዘርይሁን የልብወለድ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት፣ ጋዜጠኛ ነበር።
የድርሰት ሥራዎቹ፦
► የእንባ ደብዳቤዎች
► ድል ከሞት በኋላ
► አማኑኤል ደርሶ መልስ
► የበደል ፍጻሜ
► ጨረቃ ስትወጣ
► ብር አምባር ሰበረልዎ
► የቴዎድሮስ እንባ
► የታንጉት ምስጢር
► ማዕበል የአብዮት ዋዜማ
► ማዕበል የአብዮት መባቻ እና
► ማዕበል የአብዮት ማግስት ሲሆኑ
ተውኔቶችም፦
► ጣጠኛው ተዋናይ
► ሞረሽ
► የለውጥ አርበኞች እና
► ባልቻ አባ ነፍሶ ናቸው።
► የእንባ ደብዳቤዎች
► ድል ከሞት በኋላ
► አማኑኤል ደርሶ መልስ
► የበደል ፍጻሜ
► ጨረቃ ስትወጣ
► ብር አምባር ሰበረልዎ
► የቴዎድሮስ እንባ
► የታንጉት ምስጢር
► ማዕበል የአብዮት ዋዜማ
► ማዕበል የአብዮት መባቻ እና
► ማዕበል የአብዮት ማግስት ሲሆኑ
ተውኔቶችም፦
► ጣጠኛው ተዋናይ
► ሞረሽ
► የለውጥ አርበኞች እና
► ባልቻ አባ ነፍሶ ናቸው።
በጣም አይናፋር ነው ይሉታል። የሚሰራውን ነገር ላይ በደንብ ጥናት ያደርጋል። የተዋጣለት የታሪካዊ ልብወለድ ደራሲ ነው፦ የታንጉት ሚስጥር፣ የቴዎድሮስ እንባ፣ ማእበል(የአብዮት ዋዜማ፣ የአብዮት መባቻ፣ የአብዮት ማግስት) ምናልባት በኢትዮጵያ ታሪካዊ ልብወለድ ትልቁ ስም ብርሃኑ ዘርይሁን ሳይሆን አይቀርም። ብርሃኑ ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ብዙ መስዋዕትነት ከፍሏል። በጋዜጠኝነት ዘመኑ እውነት እውነት በመፃፉ ከስራ ታግዷል። በመጨረሻ ታላቁን የልብወለድ መጽሐፉን ሳይገላገል አልፏል።
በአፄ ቴዎድሮስ ዙሪያ የተፃፉት "የታንጉት" ሚስጥር" እና "አንድ ለናቱ" ሁለቱም ግሩም ታሪካዊ ልብወለዶች ናቸው። ለሁለቱም ደራሲያን ቁንጮ ስራቸው ይመስሉኛል።
አቤ ጉበኛ በ"አልወለድም" ልብወለድ መፅሀፉ በግዜውም ሆነ አሁን ድረስ አንገብጋቢ የሆነ ጥያቄ ቢያነሳም ለኔ እንደ ስነፅሁፍ ስራ "አንድ ለናቱ" የሚበልጥ ሆኖ ይሰማኛል። ብርሀኑ ዘርይሁንም "የታንጉት ሚስጥር"ን በፃፈበት ወቅት ችሎታው ጣራ የነካበት ወቅት ይመስለኛል። በመጀመሪያ የተፃፈው "አንድ ለናቱ" በመሆኑ ብርሃኑ ይህንን አንብቦ መፅሀፉ ጥሩ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ባለመርካቱ "የታንጉት ሚስጥር"ን ለመፃፍ እንደተነሳሳ ገልፆ መፃፉን አንድ ቦታ አንብቤያለሁ። "አንድ ለናቱ" ከልብወለድ ይልቅ ታሪክነቱ ይጎላል። "የታንጉት ሚስጥር" ግን የቴዎድሮስን ታሪክ ቀድመን አብጠርጥረነው ብናውቅ እንኳን ገና አዲስ ታሪክ እያነበብን እንደሆነ እንዲሰማን የሚያደርግ ምትሀት አለው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ብርሀኑ ዘርይሁን መፅሀፉን ሲፅፍ ታሪኩን ሳያዛባ ፣ በዛው ልክ ደግሞ ፍፁም አዲስ የሆነ የልብወለድ ታሪክ ፈጥሮ ፣ ሁለቱን ግሩም አድርጎ በማጋባቱ ነው።
በተለያየ ምክንያት ሁለቱንም ብወዳቸውም "የታንጉት ሚስጥር" ይበልጥ ይረቅብኛል። ብርሀኑ ዘርይሁን "የታሪካዊ ልብወለዶች አባት" የተባለው ያለ ምክንያት አይደለም።
ገብርዬ የቴዎድሮስ የጦር አዝማች ነው። በአሁኑ እኩያው የመከላከያ ሚኒስትር በሉት። ቴዲ ገብርዬን በጣም ይወደዋል። እንደራሱ ያምነዋል። ገብርዬም እንደዛው። ሚስቱ ተዋቡ ካረፈች በኋላ ቴዎድሮስ ቁጡ እና ጨካኝ ሆኖ ብዙ ስህተት መስራት ጀምሮ ነበር። ገብርዬን ጨምሮ የቴዎድሮስ ባለሟሎች ይሄን ግዜ ቴዲን ገለል ለማድረግ መከሩ። ግን እቅዳቸውን ሳያሳኩ ቴዎድሮስ ይደርሱባቸዋል። ከጁልየስ ቄሳር ልዋስና "አንተም ገብርዬ አንተም" ያሉ ይመስለኛል። "ገብርዬ አንተኮ የኔ ነህ። እነሱ ከፈለጉ የራሳቸውን ገብርዬ መፍጠር ይችላሉ።"
ወደ ዋናው ታሪክ ደጉ ዘመን ልመልሳችሁ
ታሪኩ የሚጀምረው ቴዎድሮስ ወደ ጎንደር ሲገቡ ነው። ታንጉትም ከባሏ ጋር አብራ ወደ ጎንደር ትመጣለች። ታንጉት የቴዎድሮስ ዘመድ የገብርዬ ሚስት ናት። ቴዎድሮስ ራሳቸው ናቸው የዳሩለት። ታንጉት በጎንደር ሴቶች ውበት ትደነግጣለች። ባሏን የሚያማልሉባት የሚነጥቋት ይመስላታል። በዚያ ላይ ልጅ መፀነስ እንቢ አላት። አዋቂ ቤት ስትሄድ መውለድ የማይችለው ባሏ መሆኑ ተነገራት። እዚህ ጋር ከባድ ውሳኔ ትወስናለች። በድብቅ ከሌላ ወንድ ማርገዝ። ይሁን እንጂ ይህንን ስትፈፅም በደብተራ አክሊሉ አይን ውስጥ ገባች። ለመሆኑ ደብተራ አክሊሉ ማነው?
ደብተራ አክሊሉ እና ቴዎድሮስ አብሮአደጎች ናቸው። በልጅነት የገና ጨዋታ ላይ ከቴዲ በተሰነዘረች ሩር ደብተራው የዘር ፍሬውን አጥቷል ። ደብተራው ማግባት መውለድ አይችልም። በዚህም ቴዲ ላይ የማይበርድ ቂም ይዟል። ቴዲን በተለያየ ተንኮል ለማጥቃት ነገር ሲገነግን ነው የሚውለው። ለተንኮሉ የደጃች ክንፉ ልጅ፣ ልጅ ጋረድ ይተባበረዋል። ሁለቱ ሰዎች ለየቅሉ ቢሆኑም የጋራ ጠላታቸው አስተሳሰራቸው―ቴዎድሮስ። አሁን ደግሞ በረከት ደጃቸው ድረስ ሰተት ብሎ መጥቷል―የታንጉት ሚስጥር።
ልብወለዱ በታንጉት ሚስጥር እየተዘወረ የመጨረሻው ገፅ ድረስ ይፈሳል። በጥቂት መነሻ የተነሳች ነገር እንዴት ሃገር ልትፈርስ እንደሚችል ማየት ይቻላል። ትንሽ ምላጭ ሃገር ትላጭ እንዲሉ። በአጠቃላይ መፅሀፉ ባህልነ፣ ስነልቡና እና ታሪክ ተጣጥመው የተሰናኙበት ምርጥ ታሪካዊ ልብወለድ ነው።
(ታንጉት እና ደብተራ አክሊሉ የፈጠራ ገፀባህሪያት ናቸው)
ማስተርፒስ የአንድ ደራሲ ታላቁ ስራው ነው።በዚህ ስሌት የሐዲስ አለማየሁ ማስተርፒስ "ፍቅር እስከ መቃብር"፣ የበአሉ ግርማ ደግሞ "ሐዲስ" ናቸው ለኔ። የአዳም ረታ ትንሽ ሊያከራክር ይችላል―ከ"ግራጫ ቃጭሎች" እና ከ"የስንብት ቀለማት"። ዛሬ የማወራው ግን የደራሲው ብቻ ሳይሆን የአማርኛ ስነፅሁፍ ማስተርፒስ ስለሆነው "የታንጉት ሚስጥር" ነው።
ይህ ታሪካዊ ልብወለድ እፁብ ድንቅ ነው። መቼቱን የአፄ ቴዎድሮስን ኢትዮጵያ ያደረገው ልብወለድ አስደናቂ ታሪክና ረቂቅ ምናብን ያስተሳሰረ ነው። አቤ ጉበኛ ቀደም ብሎ የቴዎድሮስን ታሪክ "አንድ ለናቱን" ቢያቀብለንም በብዙ መስፈርት ብርሃኑ ዘርይሁን የበለጠ ታሪካዊ ልብወለድ ሰጥቶናል።
በመጽሐፉ ሚስስ ሮዜንታል የምትባል ገፀባህሪ አለች።
ሚስስ ሮዜንታል ሕይወቷ ከእነእስተርን ሚስዮናዊ
ሕይወት ጋርየተቀናጀው፤ በሃይማኖታዊ ስሜት፤ ወይም በሐዋርያዊ መንፈስ አልነበረም። ሕፃን ሆና ስንኳ፤ እንደ መሰሎቿ የቤተክርስቲያን ሥርዓት አይማርካትም ነበር። ሌሎች ልጆች እሑድ መጥቶ የክት ልብሳቸውን ለብሰው ቤተክርስቲያን የሚሔዱበትን ጊዜ በጉጉት ሲጠብቁ ሮዜንታል ስለ እሑድ የምታልመው፤ ከቲአትር ቤት ጋር
በተያያዘ መንገድ ነበር። ግን የሚስባትና የሚማርካት ተውኔት ሳይሆን በተለይ ለሴቷ ተዋናይ ተመልካች
የሚሰጠው አድናቆት ነበር። ከዚህም የተነሳ፤ ወጣትዋ ሮዜንታል ኻያ ዓመት እስኪሞላት ድረስ እየተፈራፈቀ
ካደረባት ብዙ ዐይነት ምኞት ዋናው፤ በድፍን አውሮፓ ስሟ የተጠራ ተዋናይ መሆን ነበር። ተውኔት ትምህርት ቤት ገብታ ሞከረች፤ አልሆነላትም። አስተማሪው አንድ ሳምንት ከፈተናት በኋላ፤ ‹ያንቺ ችግር ምን መስለሽ? ቲአትር ከመጫወት ይልቅ በሐሳብሽና በስሜትሽ ለራስሽ ነው የምታጨበጭቢው› ሲል አሰናበታት። ከዚህም አንድ ልዑል አግብታ ልዕልት ለመሆን ተመኘች። ስንኳን ልዑል ደኅና ከበርቴ ባል አላጋጥማት አለ። ያልተሳካ ምኞት፤ ወደ እውን ያልተለወጠ ሕልም፤ ብስጭትጭት፤ ቅብጥብጥ
እያደረጋት በሔደበት ወቅት ነበር ከሚስተር ሮዜንታል ጋር የተገናኘችው። በውበቱም ሆነ በቁመናው
ይማርከኛል በፍቅር ‹ይወድቅልኛል› ብላ ያሰበችው ወንድ ዐይነት አይደለም። አፉ የጉጉት የመሰለ ነው።
ስብከት የሚያሰማበት ድምፁ ሳይቀር ያለልክ እንደተወጠረ ጅማት ሲጢጥ የሚል ይመስላል። ሚስዮኑ ከሚካፈለው አበል በቀር ሌላ ሀብት የለውም። ነገር ግን፤ ለስብከተ ወንጌል ኢትዮጵያ ወደሚባል የጥቁር ሕዝቦች አገር እንደሚሔድ ሲነግራት፤ ለተቀጨ ምኞቷ መካሻ ዕድል የቀረበላት ሆኖ ተሰማት። ነጭ ልዑል ልታገባ ባትችል በደንቆሮ ጥቁር ሕዝብ መካከል እንደ ልዕልት ትከበራለች። በግሩም ተዋናይነቷ የሚያጨብጭብላት፤ የሚያደንቃት፤ ‹ፊርማዋን የሚለምናት› ተመልካች በአውሮፓ ባታገኝ፤ በአክብሮት የሚሰግድላት ጥቁር ሕዝብ ይኖራታል። ብዙ ዓመታት ቆይታ እንደገና ወደ ሀገርዋ ስትመለስም፤ እስከ
ዓለም ዳርቻ ተጉዛ ስለ ፈጸመችው ገድል፤ ስለ አዳነችው ነፍስ ስትተርክ ሰው ሁሉ በአድናቆት ያዳምጣታል። ሚስተር ሮዜንታልን አግብታ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ለዚህ ስትል ነበር።
ወደ ኢትዮጵያ ከመጣች በኋላ ያጋጠማት ሁናቴ ግን እንደ ገል ፍርክስክሱን አወጣባት። ጭርንቁስ ከለበሰ ደሃ ገበሬ አንሥቶ የሚያደንቃትን፤ የሚሰግድላትን ቀርቶ አንዳችም የተለየ ግምት የሚሰጣት ሰው አላገኘችም። በንጣትዋ፤ በአለባበስዋ እንደ ጉድ አይተዋት፤ ተቀላልደው፤ ተሣሥቀው ገልመጥ ገልመጥ ብለው ተመልክተው ያልፉዋታል። መጀመሪያ ላይ ምናልባት ቀደም ሲል ዐረቦችንና ቱርኮችን በማየታቸው በቆዳ ፍካት አንድ መስያቸው ቢሆን ነው ስትል ራስዋን አጽናናች። ከየት አገር እንደመጣች፤ ማን እንደሆነች ለምን ከፍተኛ ተግባር እንደመጣች ቀደም ሲል ከሚስዮኖች ጋር ቆይተው አንዳንድ እንግሊዝኛ ቃላት በሚሞክሩ አስተርጓሚዎች አማካይነት ማስረዳት ባዳ በመሆንዋ ያዘኑላት ይመስል ብቻ ከንፈራቸውን ይመጡላታል። ከራሳቸው ዝቅ አድርገውም ባይሆን ከራሳቸው ቅንጣት ያህል ከፍ አድርገው እንደማይመለከቱዋት ሲታወቃት ትበሽቃለች። ትበግናለች። ግን ሕልሟ ሁሉ እንደ ጉም በንኖ መቅረቱን መቀበል ስለማትፈልግ ምርጥ ቀሚሷን ከነመደረቢያ ካባዋ ትለብስና፤ እንደ ምኞትዋ ልዕልት፤ ቀጥ፤ ጅንን፤ ኮስተር ብላ መሔድ ስትጀምር፤ ጉምጉምታው ሣቅን ለማፈን ይመስል አፍን በመዳፍ መክደኑ ይበዛል።
በንዴት ምክንያት ትጠይቃለች። «ምን ነካት ሴትዮዋ? የሙቀጫ ልጅ ውጣለች እንዴ እንደዚህ የደረቀችው?» ብለው እንደሚቀልዱ ይነገራታል እርር ትላለች።
ተስፋ ባለመቁረጥ የምትፈልገውን ከበሬታ ለማግኘት ስትል ወደ ሌላው ጫፍ አቀራረብ ትሔዳለች። መናኛ ለብሳ፤ ራስዋን ሸፍና ጎንበስ ብላ አንገቷን በመድፋት፤ የጥቁር ሕዝብ ነፍስ ለማዳን ሕይወትዋንና የድሎት ኑሮዋን የሠዋች ለመምሰል ትሞክራለች። ውጤቱ ካሰበችው የተገላቢጦሽ
ይሆንባታል። ‹ኧረ ይች የውጭ አገር እንግዳ አንጀትዋ ታጥሮ ልትወድቅ ምንም አልቀራት!› ከጥራጥሬ
እስከ ሙክት ድረስ ምግብና መጠጥ ይላክላቸዋል። ከዚያኛው ያላነሰ ያናድዳታል።
‹ደደቦች፤ ምንም የማይገባቸው ፍጹም ደደቦች› ትላለች፤ ከራስዋ ጋር። ከመብሸቅዋ የተነሣ፤ እርሷ የሚሰማትን የበላይነት ሊረዱት አለመቻላቸውን ከድንቁርና ዐልፎ እንደ ወንጀልም ልትቆጥረው ይቃጣታል። ሌላው ቀርቶ፤ ብዙ ጊዜ አብራቸው በመገኘት እንዲከተሉዋትና እንዲያጅቡዋት የምትፈልገው፤ በክርስቲያኖች ዘንድ ዝቅ ተብለው የሚታዩት ፈላሾች እንኳ የተለየ አክብሮት አያደርጉላትም። ልታስተምራቸው፤ ልታስረዳቸው የምትፈልገውን ነገር በትሕትናና በጥሞና አዳምጠው፤ ዐልፎ ዐልፎም ፈገግታ እያሳዩ ያለ አንዳች መርበድበድ ወደ የግል ሥራቸው ይበተናሉ። የፈረንጁን ጥልፍ ሥራ ስታሳያቸው በበኩላቸው ፈትል ይዘውላት ይቀርባሉ - ሊያሳዩዋት፤ ሊያስተምሩዋት። ሹራብ ሥራ አሳይታቸው ስትጨርስ እየመሩ ወደ መንደሩ ሸማኔ ይወስዱዋታል፤ እኛም አለን የማለት ዐይነት። ከርስዋ
ችሎታ ጋር ውድድር መያቸው ያበግናታል።
፨፨፨
የኢትዮጵያውያን ስነልቡና ከአድዋ በፊትም ሆነ በኋላ እንዲሁ ነበር። ለነጭ የሚሰግድ አልነበረም። ምናልባት አድዋ ያደረገው ነገር ቢኖር አውሮጳውያኑ ይህንን እውነታ ከሽንፈት ጋር መጋታቸው ነበር። በቆዳዬ ምክንያት የተለየ ክብር አገኛለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ከካርታው ላይ ከኢትዮጵያ ሌላ ሃገር መፈለግ አለበት። ምክንያቱም ይህ
የቴዎድሮስ ሃገር ነው!
የዮሐንስ ሃገር ነው!
የሚኒሊክ ሃገር ነው!
የአድዋ ሃገር ነው!!
GOOD AND EVIL (and beyond)
ቴዎድሮስ ታላቅ የበጎነት ሐይል
በቴዎድሮስ ዕንባና በየታንጉት ሚስጥር ውስጥ እኩይ ገጸ ባህሪ የነበረው ደብተራ አክሊሉ ምንም እንኳን የፈጠራ ውጤት ቢሆንም በስነ ጽሁፍና በሌሎች የጥበብ ዘርፎችም እንደተለመደውና እንደሚዘወተረው በአንድ ወቅት የሚኖረውን መንፈስ በአንድ የፈጠራ ገጸ ባህሪ ጠቅሎ ለማንጸባረቅ የሚደረግ ጥረት አካል እና አብይ አብነትም ጭምር ነው።ጥበብ ነውና አይቆረፍደንም፤እንዲያውም ለምናነበው ልብወለድ፡ለምናየው ተውኔት፡ለምናደምጠው ግጥም ውበትና ጉልበት ይሆናል።እናም በደብተራው ውስጥ የቤተ ክህነቱን ጉርምርምታ፡የአብሮአደግን ቂም፡የወታደሩን ቅሬታና ብሶት(በደብተራው ጓደኛ ጋረድ በኩል) እናነባለን።እንደውም ደብተራው ጋረድን እንደልቡ ስለሚዘውረው ጋረድ በሁለት እግሩ ራሱን ችሎ የቆመ ሰው አይመስለኝም፤በሌላ ሰው አካል ውስጥ ያለ የደብተራው ቅጥያ እንጂ! ካላችሁማ አክሊሉ በልጅነቱ ከልጅ ካሳ ጋር የገና ጨዋታ ሲጫወቱ በቴዲ እጅ የዘር ፍሬውን አጥቷል።ቴዲ ላይ ላለው ቂምም መነሻው ይኸው ነው።ታዲያ ጋረድ አእምሮውን የዘር ፍሬውን ለማዘዝ ካልሆነ ለሌላ ሲጠቀመው አላስተዋልኩም።በቃ ጋረድ ማለት አክሊሉ የጎደለው የሰውነት ክፍል "የአክሊሉ የዘር ፍሬ" ማለት ነው።
ጋረድና አክሊሉ አብረው አይደለም የሚገነግኑት!ደብተራው ተንኮሉን ለብቻው ነው የሚቀምመው።ብርሀኑ ዘርይሁን ጋረድን የፈጠረበት ምክንያት ሁለት ይመስለኛል።አንደኛው የአክሊሉን ሀሳብ አእምሮው ውስጥ ገብቶ ከሚያሳየን ከጋረድ ጋር ሲያወሩት እኛ እንድንሰማው ነው-I think it is louder this way! ይህ እንግዲህ ስነ ጽሁፍ ይባላል።ከinterior monologue(ውስጣዊ መነባነብ) ይልቅ ደራሲው የመረጠው ይህን መንገድ ስለሆነ በራሱ መጽሀፍ "ለምን?" አንለውም!አበጀህ እንጂ! ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ አንድን ገጸ ባህሪ በአንድ ግዜ ወታደርና የቤተ ክህነት አገልጋይ ማድረግ ስለማይቻል ነው።ይሄ እንግዲህ ስም የለውም!በተረፈ ግን በቴዲ ዘመን የነበረው በካሳና አገዛዙ ላይ የተቀሰረው አሉታዊ አስተሳሰብ ሁሉ እንደ ዛር ተጠቅልሎ በደብተራው መንፈስ ውስጥ የሰፈረ ይመስለኛል።
በበጎና በክፉ መሀል ያለ የማያቋርጥ ጦርነት(ትግል) ለዘመናት የስነ ጽሁፍ፡የፍልስፍና እና የሀይማኖት ዋና መዘወርያ ሆነው ኖረዋል፤ ከሁሉም በላይ ግን የራሷ የህይወት ምክንያትና ውጤት ይመስሉኛል።በተፈለገው መጠን ብትደቁ፤ በምትችሉት አቅጣጫ ብትረቁ ይህ እውነት ጥርሱን አግጦ፡አይኑን አፍጦ ይጠብቃችኋል።በየታንጉት ሚስጥር ውስጥ በአብዛኛው በጎን የሚወክለው ቴዲና አገዛዙ ስለሆነ ብልጫ አለው፤ አሁን ግን መንግስት ክፋትን እየወከለ ተስፋ ሊያስቆርጠኝ ይሞክራል! እስካሁን አልተሳካለትም እንጂ!
በአንድ ወቅት ASTRO BOY የተሰኝ የANIMATION ፊልም ተመለከትኩ።ላሳጥርላችሁና በፊልሙ ላይ አንድ ሮቦት ገጸ ባህሪ ቀና መንፈስ ያለው ሆኖ ተቀርጾአል።ያው እንደተለመደው ይህ ሮቦት ክፋትን ያሸንፋል በስተመጨረሻ!
"ጥሩ ሮቦት አለ ሊሉን ፈልገው ነው?"አልኩኝ ፊልሙ እንዳበቃ።
"አይደለም!" አለኝ ፊልሙን አብሮኝ የተመለከተው ጓደኛዬ "ምንግዜም ጥሩ መጥፎን ሊያሸንፍ፡ በጎ ክፋትን ሊረታ ፡ ቀና ጠማማን ሊያቀና ሀይል እንዳለው ሊነግሩን እንጂ!"
እና በጐነት ሀሳብ ነው፤ሁሌ የሚያሸንፍ! ጠመንጃ አይደለም የሚያሸንፈው።መሳሪያ እኮ በበጎውም በክፉውም እጅ አለ።ቃታውን ለሳበ የሚተኮስ ምርጫ አልባ ግዑዝ ነው!ጠመንጃ የሚያሸንፍ ቢሆን ኖሮማ ቴርሞፓይሌ ላይ እነዛ ምርጥ 300 የስፓርታ ወታደሮች እልፍ አእላፉን በሚሊዮን የሚገመተውን የፋርስ ጦር እንዴት ገትረው ያዙት!
ምስጢሩ ቀላል ነው።በአይናችን የማይታዩ ሀይሎች ናቸው ሲዋጉ የነበሩት።ምንም ይከሰት ምን ምትሀታዊው ቀናነት ሁሌም ድል ይነሳል!
በጣም ሀሳባዊነት ያጠቃዋል እንጂ ከዚህ የላቀ ጽንሰ ሀሳብ ደግሞ አለ፦"ከህሊና በላይ" ብዬ ብሰይመውስ(for a detailed analysis of this concept read "BEYOND GOOD AND EVIL" by FRIEDRICH NIETZSCHE) ነገር ግን አሁን እየኖርንበትና እየሞትንበት ላለው አውድ ተጨባጭ እውነት አይሆንልንም።we are not yet "beyond".We are under the realm of good and evil.ትንሽ እንድፈላሰፍ ይፈቀድልኝ!
Shakespeare articulated "There is no good and evil,it is your thinking that makes it so!"
ይህ ማለት ማሰብ እስካላቆምን ድረስ ምንግዜም ነገሮችን፡ ሰዎችን፡ ክስተቶችን ጥሩና መጥፎ ብለን መፈረጃችንን አናቋርጥም! የዚህ ሁሉ ዝባዝንኬ ምክንያት ደግሞ የማሰቢያው አካላችን(አእምሮአችን) ነው።ታዲያ አእምሮ የማሰብ ስራውን የሚያቆመው መቼ ነው? ጥሩው ዜና ስንሞት ብቻ አለመሆኑ ነው!
I shall stop now! I went way too far! And because I remembered a verse from the Bible-
ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም፥ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል።
መጽሐፈ መክብብ 12:12
And further, by these, my son, be admonished: of making many books there is no end; and much study is a weariness of the flesh.
Ecclesiastes 12:12
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ