ልጥፎች

ከኖቬምበር, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአዳም ረታ ትርክትና ስነ ፅሑፍ

ምስል
  የአዳም ረታ የወል ትርክትና ስነ ፅሑፍ በአብርሃም ገብሬ ደራሲ አዳም ረታ በልብ ወለዶቹ ውስጥ የኢትዮጵያን ፍልስፍና፣ ታሪክ፣ ማህበራዊ መስተጋብር እና የወል ዕሴቶችን በምልዓት ዳስሷል፡፡ የኢትዮጵያን ከፍታና ዝቅታ፤ የህዝቡን ደስታና እዝነት በውብ የአጻጻፍ ይትበሃል አስነብቦናል፡፡ ግለሰባዊነትን ከማህበራዊ ማንነት ጋር እያዛመደ ኑረታችንን ሂሷል፡፡  አዳም ረታ የመጀመሪያ አጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ ከሆነው ማህሌት̕ ድርሰት በ1981 ዓ.ም ካሳተመበት ጊዜ አንስቶ አፍ̕  የተሰኘው ስግር ልብ ወለድ እስካሳተመበት 2010 ዓ.ም ድረስ ስድስት አጫጭር እንዲሁም አራት ረዥም ልብ ወለዶችን ለተደራሲያን አብቅቷል፡፡ በእነዚህ ድርሰቶቹም ከፍ ያሉ ፍልስፍናዊ ዕሳቤዎችንና ማህበራዊ ሂሶችን አስነብቦናል፡፡ በተለይ ታሪክ፣ ማህበረሰባዊ መስተጋብር፤ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን፣ የሰው ልጆችን የህልውና እና የዕጣ ፈንታ ጉዳዮችን በልብ ወለዶቹ ውስጥ በምልዓት ተዳስሷል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ኢትዮጵያዊ የሆኑ የወል ፍልስፍናዊ እሳቤዎችን አጉልቶ በማሳየት ረገድ አዳም ረታ ከፊተኛው ረድፍ ላይ የሚቀመጥ ደራሲ ነው፡፡ በተለይ ደራሲው ወደ በኋላ አካባቢ በታተሙ ስራዎቹ ውስጥ በኢትዮጵያዊ እይታዎች የተቃኙ ፍልስፍናዊ ዕሳቤዎችን በስፋት አስተዋውቋል፡፡ በተለይም በ‘እቴሜቴ የሎሚ ሽታ’፣ በ ‘ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ’፣ በ‘የስንብት ቀለማት’ እና በ‘አፍ’ ውስጥ እነዚህን ፍልስፍናዊ ዕሳቤዎችና ማህበራዊ ሂሶች ጎልቶ የተንጸባረቀባቸው ልብ ወለዶች ናቸው፡፡ በዚህ አምድም ደራሲ አዳም ረታ በፈጠራ ድርሰቶቹ ውስጥ የወል ማንነት፣ ዕሴትና ሀገራዊ ተረክ ለመስራት ያደረገው ኪነ-ጥበባዊ ሃሰሳን በጨረፍታ ልናስቃኛችሁ ወድደናል፡፡ ያልተሄደበት የደራሲው መንገድ ኪነ ጥበ...