ልጥፎች

ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ጃንሆይ ምን ተናገሩ?

ምስል
  ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ . ም ጃንሆይ ምን ተናገሩ ? Wednesday, 04 May 2016 / በሰንደቅ ጋዜጣ የታተመ / በ ጥበቡ በለጠ *************************************  ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ . ም በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ የተለየች ዕለት ነች። ምክንያቱም አንድ ንጉሥ በጠላት ወታደሮች ሐገሩ ተወርራ፣ የሚያደርገው ቢያጣ ከሐገሩ ውጭ በባዕድ ሀገር ተሰድዶ፣ በመጨረሻም ከአምስት ዓመታት በኋላ በውጭም በውስጥም ድል አድርጎ ወደ ሐገሩ በመምጣት፣ የጠላቶቹን ባንዲራ አውርዶ፣ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ የሰቀለ፣ ከዚያም ለሐገሩ ሕዝብ ንግግር ያደረገባት ዕለት ፈፅሞ የተለየች ነች። ኢጣሊያ በ 1888 ዓ . ም አድዋ ላይ በግማሽ ቀን ጦርነት የውርደት ማቅ መከናነቧ ሲቆጫት ሲያንገበግባት ኖሯል። እናም ከ 40 ዓመታት በኋላ በ 1929 ዓ . ም ቂሟን ለመወጣት ኢትዮጵያን ወረረች። ኢትዮጵያ ደግሞ ገና የሽግግር ወቅት ላይ የነበረች በመሆኑ የተደራጀ መንግሥት እና ጦር አልነበራትም። ፋሽስት ኢጣሊያ ደግሞ አሉ የተባሉ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን መርዝ ከሚተፉ አውሮፕላኖች ጋር ይዛ ኢትዮጵያን ወረረች። ወረራው የተደራጀ ስለነበር በቀላሉ ሊቀለበስ አልቻለም። ስለዚህ ንጉሠ ነገስቱ እዚሁ ሆነው የከፉ ነገር ከሚመጣ ወደ ውጭ ወጥተው መታገልን የዘመኑ ሹማምንቶች እንደ አማራጭ መከሩ። እናም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከመንበረ ስልጣናቸው ተነስተው ኢትዮጵያን ለቅቀው ወደ እ...