እራስን መሆን/ እኔ ማን ነኝ?
አንድ ጊዜ ኮሌጅ እያለሁ አንዱ ፕሮፌሰር ሁላችንን እንዲህ ሲል ጠየቀ ” ከእናነንተ ውስጥ ቶሎ ወይ በቀላሉ የሚናደድ ማን ነው?” ክፍል ውስጥ ከነበርነው 25 የምንሆን ተማሪዎች ውስጥ ከስምንት እስከ አስር የሚያክሉ ተማሪዎ እጃቸውን አወጡ። ፕሮፌሰሩም መልሶ ጠየቀ ” እስቲ ማን ይነግርኛል ለምን በቀላሉ እንደሚናደድ?” የዛን ጊዜ ተማሪው ሁሉ ጸጥ አለ። ከዛን ፕሮፌሰሩ ያለው አይረሳኝም። “እዚህ ውስጥ እድሜው ከ20 በታች ያለ ተማሪ ያለ አይመስለኝም፥ ታዲያ ቢያንስ ሃያ አመት ያህል ከራሳችሁ ጋር ኖራችሁ ስለራሳችሁ በደነብ እንዴት ነው የማታውቁት? በቀላሉ ስትናደዱ ለምንድን ነው በቀላሉ ምናደደው ብላችሁ እንኳን እንዴት አትጠይቁም” አለ። ይህ ለብዙዋችን እውነት ነው፥ከእራሳችን ጋር ይህን አመት ስንኖር የምናደርገውን ነገር ለምን በለን አንጠይቅም።ስለ እራሳችን ምን ያህል እናውቃለን? እኛ ስለራሳችን ካላወቅን ሌሎች ስለኛ ሚሉትን ብቻ አሜን ብለን እንቀበላለን።
እራሳችን ማን እንደሆንን ሳናውቅ እንዴት እራሳችንን እንሆናለን? እራስን ማወቅ ማለት ምን ማለት ነው። ከልጅነታችን ጀምሮ የተለያዩ ነግሮች ከቤተስብ፥ ትምህርት ቤት፥ ጓደኞች እና ባጠቃላይ ህብረተሰብ ስለራሳችን ስንሰማ ነው ያደግነው። ባካባቢያችን ያሉ ሰዎች በዘራችን፥ በቆዳ ቀለማችን፥ በትምህርት ቤት ባለን የትምህርት ውጤት፥ በቤተሰቦቻችን የንብረት መጠን ብቻ በተለያዩ ነግሮች ተነስተው ማንንታችንን ይነግሩናል። እኛም የሰማነውን ተቅብለን ያ ያሉኝ ነኝ ብለን እንኖራልን። በእርግጥ ልጅ እያለን የሚነገረንን ሁሉ ከመቀበል ውጪ ነገሮችን አመዛዝኖ እና አጣርቶ የመቀበሉ ጥበቡ አልነበረንም፥ ነገር ግን ካደግን በኃላ ግን እራሳችንን ማወቅ የሚገባን ከሰው ከስማነው ብቻ ከሆነ እራሳችንን ሳይሆን ሌላ ስውን እየኖርን ነው።
እኛ ማን እንደሆንን ሳናውቅ ስንቀር ሰው የጠንን ማንነት ተሸክመን እኖራለን። ሴት ስለሆንሽ ይሄን ማድርግ አትቺይም፥ ወይ ወንድ ስለሆንክ ይህን ማድረግ የለብህም፥ የመጀመሪያ ልጅ ስለሆንክ ይህን ወይ ያን ማድረግ አለብህ፥ ዘርህ ይህ ስለሆነ እንዲህ እና ያን ማሰብ አለብህ፥ ብር ስለሌለህ ይህን ወይ ያን አታቅድ አታስብ •••
ሰው ማን እንደሆንን ሊነግሩን አይገባም ሲባል ባጠቃላይ ሰው አንሰማም ማለት አይድለም።እግዚአብሔር ይመስገን በሒይወታችን እንዲመሩን፥ መልካሙን መንገድ እንዲያሳዩን፥ ከእነርሱ ሒይወት እንድንማር ስላስቀመጣቸው ሰዎች። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ” ሞኝ ከራሱ ውድቀት ጠቢብ ግን ከሌላው ይማራል” ምክርን እና የሒይወት ምሳሌን እየተማርን ሂይወታችንን ምሻሻል ይኖርብናል።ነገር ግን የሰው ሃሳብ እና ቃል የኛን ማንነት መወስን የለበትም። ማን ነኝ ወይ ምን ማድረግ እፍልጋልሁ ብለን ስንጠይቅ የምናስበው ስዎች ምን እንዳሉን ወይ ከኛ ምን እንደሚጠብቁ ከሆነ ያኔ ስተናል።
ታዲያ እራስን ማወቅ እንዴት ይቻላል?
እራስን ማግኘት ወይ እራስን ማወቅ ማለት ለምንስማው፥ ከምናየው እና ከምናነበው እንዴት ሊያልፍ ይችላል። እነዚህ ነጥቦች እራሳችንን እንድናውቅ ይረዱናል።1. ውስጣችንን መስማት. እግዚአብሄር ሲፈጥረን ህሊናችን ከሱ ሃሳብ ጋር እንዲስማማ አድርጎ ነው። የተሳሳተ ነገር ስናደርግ ብዙ ጊዜ ህሊናችን ይወቅስናል፥ ውስጣችን ደስ አይለውም። አንድ ነገር ስናደርግ ውስጣችንን መጠየቅ ፥ ውስጤ ምንድን ነው ሚስማኝ? ምንድን ነው እግዚአብሔር ለውስጤ ሚናገረው ብለን መጠየቅ እናም ከዛ ከሚሰማን ነገር ወይ የውስጥ ድምጽ ጋር መስማማት። ያልሆነውን ስናስመስል ውስጣችን ምቾት አይሰማውም፥ ምክንያቱም ውስጣችን ያለው ድምፅ እግዚአብሔር የእርሱን ባህሪ እንድንወርስ ከማንነታችን ጋር ያያዘው ስለሆነ ነው። ስለዚህ ለራስ ታማኝ መሆን፥ አባቴ ወይ ጎረቤቴ ምን ያላል ወይ ከኔ ይጠብቃል ከማለታችን ይልቅ እግዚአብሔር የሰጠኝ ህሊናዬ የውስጥ ድምጼ ምን ይላል ብለን መጠየቅ። አንድ አንዴ ውስጣችን የሚለንን ስምቶ ለዛ መታዘዝ ይከብደናል ምክንያቱም እድሜ ልካችንን የኖርነው የውጭ ድምጽ እየስማን ስለኖርን። ከራሳችን ጋር እንስማማ።
2. የራስን ዋጋ ማወቅ. ስንፈጠር እኛን የመስለ ሌላ አልተፈጠረም። በእግዚአብሔር እያንዳንዳችን ልዩ ሆነን ነው የተፈጠርነው። የአንድ ስው ዋጋ በምንም በማንም አይለካም። ይኛ ዋጋ የፈለግነው ነገር ሲሳካ አይጨምርም ወይ ስንደክም ወይ ስንወድቅ አይቀንስም። ሃብት፥ውበት፥ትምህርት ደረጃ፥የትውልድ ስፍራ እና ዘር ዋጋችንን አይጨምረውም ወይ አይቅንሰውም። የሰው ሁሉ ዋጋ እኩል ነው ግን ያንዱ ሌላውን አይተካውም። ስለዚህ እኔ ይሄ ስለሌለኝ ወይ ስላለኝ መደሰት፥ መከበር ወይ በሰላም መኖር አይገባኝም አንበል። ሰው ለኛ ሚሰጠን ዋጋ ሳይሆን እኛ ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ነው ወሳኝ ነገር። አብዛኛው ጊዜ ሌላው ሰው የሚሰጠን ዋጋ እኛ ለራሳችን ከሰጠነው ዋጋ ጋር አንድ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የፕሬዝዳንት ኦባማ ዋጋ እና መንገድ ላይ የሚተኛው ወንድማችን ዋጋ አንድ ነው።
3. አይምሮን ማደስ. ከልጅነታችን ጀምሮ ስለኛ ብዙ ተነግሮናል። ያንን እንደ እውነታ ወስድን ሳናስብው ማንንታችን እድርገናችዋል። አሁን ግን ቆም ብለን ስለኛ የምናስባችው ነገሮች ከየት እንደመጡ እንመርምር እና ለኛ የማይጥቅሙን ነግሮች ሁሉ እናስወግድ። አንተ እኮ ፈሪ ነህ፥ ትምህርት አይገባህም፥ ጸባይህ ለሰው አይገባም፥አትረባም፥መልክህ አያምርም፥ መናገር አትችልም ዝም በል፥ ካንተ ያ ወይ ይሄ ይሻላል፥ አይሳካላልህም፥ የተለያዩ መጥፎ እና ማንነታችንን በመጥፎ ሊቅይሩ የመጡ ንግግሮችን ሁሉ ከአይምሮአችን አጥቦ ማውጣት። ትዝ ይለኛል የተውስኑ ልጆች ጋር ቁጭ ብለን ስናወራ ስለራሳችሁ መጥፎ የምታስቡት ነገር ከየት እንደመጣ አስቡ እስቲ ስላችው ሁሉም ልጅ እያሉአንድ ሰው የተናገራቸው ነገሮች ነበሩ። እኛ ግን ሳናስተውል እራሳችንን በእነርሱ ቃሎች ወስነነዋል። ወይም ሰዎች ባይሉን ደግሞ አንድ አንዴ እኛ እራሳችን ካለፍንባቸው የድሮ ድካሞች ዛሬያችንን ወስነነዋል። ስለዚህ ቆም ብለን እንዚህን ሃሳቦች በመልካም ሃሳቦች እንተካቸው።
4. ነገሮችን እና እራስን መለየት. በአካባቢያችን የሚሆኑ ነግሮች የራሳቸ ማንነት አላቸው የነሱን ማንነት ከእኛ ጋር አለማያያዝ። ለምሳሌ ትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ሳናመጣ ስንቀር ያንን ወስደን እኔ ማለት ሰነፍ ነኝ ወይ እንዲህ ነኝ ከማለት በፊት ትምህርቱን ጥሩ ውጤት ላመጣ የሔድኩበት መንገድ ጥሩ አልነበርም ስለዚህ በሚቅጥለው በየትኛው መንገድ ልሂድ ብሎ ማሰብ። ባጠቃላይ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ከመደምደም በፊት እንዴት ያንን ነገር ልስራው ወይ ላሻሽለው ብሎ ማሰብ። ሌላ ምሳሌ ከሰው ጋር ያለን ግንኙነት መልካም ካልሆነ አይ እኔ ጥሩ ጓደኛ አልሆንም ከማለት በፊት ነገሩን ከራስ ማንነት ወጣ አድርጎ በምን መንገድ መግባባት እንችላለን፥ ምን ብናደርግ ይሄ ይስትካከላል ማለት አለብን።
5.እራስን ከሌላው ጋር አለማወዳደር. ከላይ እንዳልነው ሁላችን ስንፈጠር ልዩ ልዩ ሆነን ነው። የሌላው ሒይወት ለመማሪያ ምሳሌ ሊሆነን ይገባል እንጂ ማወዳደሪያ ምስፈርት መሆን የለብትም። ሰው ሁሉ በየራሱ የሚሄድበት መንገድ አለው ፥ ያንተ መንገድ ከሌላው ይለያል፥ የሰው መንገድ ላይ መግባት አንተ መድረስ የሚገባህ ቦታ አያደርስህም። አንተ ማድርግ በምትችለው እና እግዚአብሔር በሰጠህ ነገር መዝነው ። መጽሃፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር ለሁሉ የተለያየ ችሎታ ወይ ተሰጥኦ እንደሰጠ ግን እያንዳንዱ ሚጠየቀው በተሰጠው በዛ ነገር ምን እንዳደረገ ነው። የሌላውን ሰው ስጦታ ትተን ይኛ የተሰጠን ላይ ማተኮር።
6. መልካምን ማሰብ ጥሩ ጥሩ ንገሮችን ማሰብን አይምሮአችንን ማስለመድ። ብዙ ጊዜ ለሰው ምንለውን እንጠነቀቃለን በቃላችን እንዳንጎዳቸው ቃላት እንመርጣለን ስለራሳችን ግን ያን ያህል አንጠነቀቅም። ስለ ራሳችን የምናስበው እና ምንናገረው ነገር መልካም ንገር እንዲሆን መጠንቀቅ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ “በምላስ ላይ ሞት እና ሒይወት አለ” ይላል ለምን? ምክንያቱም በምንናገርው የሰውን መንፈስ ልንገድል ወይ ልናቀና ስለምንችል ነው። ስለራሳችን እንዲሁ በውስጣችን እንናገራለን እናስባለን ያ ሃሳብ መልካም መሆን አለበት። እራሳችንን መሆን ይከብደናል ስለራሳችን ያለን ሃሳብ መጥፎ ከሆነ። እራሳችንን ማበረታታት፥ መልካም ይሆንልሃል ፥በእግዚአብሔር የተወደድክ ነህ እያልን ብዙ ብዙ መልካም ነገሮችን መናገር አለብን።
7. እራሳችንን በስዎች አይምሮ ውስጥ አለማየት.
ብዙ ጊዜ እራሳችንን እንዳንሆን ሚያረግን እራሳችንን በሰው ውስጥ ሆነን ነው ምናየው። ማለትም ስናወራ ያ የሚስማን ሰው ስለኛ ምን እንደሚያስብ በሱ ውስጥ ሆነን እራሳችንን ማየት እንጀምራልን ከዛን መናገር የምንፈልገውን ሳይሆን መስማት የሚፍልገውን ማውራት እንጀምራለን። ይሄ በአነጋገራችን ብቻ ሳይሆን፥ ባለባበሳችን፥ ባረማመዳችን፥ በሁሉ ነገራችን በሌላ ሰው ውስጥ ያለው እይታ እንዲስተካከል እያልን እራሳችንን እንቀያይራለን። ይህ እንዳይሆን ስናወራ ወይ ስንኖር ውስጣችን እንደሚለው መሆን አልበት። ብዙ ጊዜ ውስጣችን የሚለውን መስማት ስንል መጀመሪያ ውስጣችን እግዚአብሔር ከሚለው ጋር መስማማቱን ማረጋገጥ አለብን።
**********************************************************
ምንጭ፡ - http://habeshalij.com/
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ