እራስን መሆን/ እኔ ማን ነኝ?
አንድ ጊዜ ኮሌጅ እያለሁ አንዱ ፕሮፌሰር ሁላችንን እንዲህ ሲል ጠየቀ ” ከእናነንተ ውስጥ ቶሎ ወይ በቀላሉ የሚናደድ ማን ነው?” ክፍል ውስጥ ከነበርነው 25 የምንሆን ተማሪዎች ውስጥ ከስምንት እስከ አስር የሚያክሉ ተማሪዎ እጃቸውን አወጡ። ፕሮፌሰሩም መልሶ ጠየቀ ” እስቲ ማን ይነግርኛል ለምን በቀላሉ እንደሚናደድ?” የዛን ጊዜ ተማሪው ሁሉ ጸጥ አለ። ከዛን ፕሮፌሰሩ ያለው አይረሳኝም። “እዚህ ውስጥ እድሜው ከ20 በታች ያለ ተማሪ ያለ አይመስለኝም፥ ታዲያ ቢያንስ ሃያ አመት ያህል ከራሳችሁ ጋር ኖራችሁ ስለራሳችሁ በደነብ እንዴት ነው የማታውቁት? በቀላሉ ስትናደዱ ለምንድን ነው በቀላሉ ምናደደው ብላችሁ እንኳን እንዴት አትጠይቁም” አለ። ይህ ለብዙዋችን እውነት ነው፥ከእራሳችን ጋር ይህን አመት ስንኖር የምናደርገውን ነገር ለምን በለን አንጠይቅም።ስለ እራሳችን ምን ያህል እናውቃለን? እኛ ስለራሳችን ካላወቅን ሌሎች ስለኛ ሚሉትን ብቻ አሜን ብለን እንቀበላለን። እራሳችን ማን እንደሆንን ሳናውቅ እንዴት እራሳችንን እንሆናለን? እራስን ማወቅ ማለት ምን ማለት ነው። ከልጅነታችን ጀምሮ የተለያዩ ነግሮች ከቤተስብ፥ ትምህርት ቤት፥ ጓደኞች እና ባጠቃላይ ህብረተሰብ ስለራሳችን ስንሰማ ነው ያደግነው። ባካባቢያችን ያሉ ሰዎች በዘራችን፥ በቆዳ ቀለማችን፥ በትምህርት ቤት ባለን የትምህርት ውጤት፥ በቤተሰቦቻችን የንብረት መጠን ብቻ በተለያዩ ነግሮች ተነስተው ማንንታችንን ይነግሩናል። እኛም የሰማነውን ተቅብለን ያ ያሉኝ ነኝ ብለን እንኖራልን። በእርግጥ ልጅ እያለን የሚነገረንን ሁሉ ከመቀበል ውጪ ነገሮችን አመዛዝኖ እና አጣርቶ የመቀበሉ ጥበቡ አልነበረንም፥ ነገር ግን ካደግን በኃላ ግን እራሳችንን ማወቅ የሚገባን ከሰው ከስማነው ብቻ ከሆነ እራ...