ልጥፎች

መንትያ ጥበባት፤ ግጥምና ሙዚቃ!

ምስል
መንትያ ጥበባት፤ ግጥምና ሙዚቃ! ሰሎሞን ተሠማ ጂ. ******************   “የአንድን አገር የሥልጣኔ ደረጃ ለማወቅ ብትሻ፤ ሙዚቃውን አድምጥ፣ ሥነ-ጽሑፉን አንብ!” ብሎ ነበር - ዲዜሬል፡፡ ፕ/ር አሸናፊ ከበደም፣ “ የአንዲት አገር ሥልጣኔ አቋም በሳይንስ፣ በፖለቲካ፣ በኤኮኖሚ፣ በቴክኖለጂና በሚሊታሪ ኃይሉ ብቻ ሳይሆን በ ሙዚቃ፣ ሥነ-ጽሑፍና በሌሎችም የኪነ-ጥበባት ዘርፎች የተደላደለ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ በተለይም ሙዚቃና ሥነ-ጽሑፍ ረቂቅ አስተሳሰብና ዲሲፕሊንን ስለሚፈጥሩ ሥልጣኔው ተስፋፍቶ መገኘት አለበት፡፡ የቴክኖሎጂና የኤኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው የረቂቁ አስተሳሰብ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሲኖሩ ነው” ይሉ ነበር (መነን መጽሔት ፣ ሰኔ 1957 ዓ.ም፤ ገጽ 22)፡፡ በማስከተልም፣ “በአዕምሮና በልብ ምንነቱ ሳይታወቅ የሚታሰብ ነገር በሙዚቃ አካል ይኖረዋል በሥነ-ጽሑፍም ግዝፎ ይወጣል፡፡ ታላቅ የተባሉት ሁሉ ዘጠና-ዘጠኝ ከመቶ የሚሆኑት የጥበባዊ (ካላሲክ) ሙዚቃ ተጨዋች የሥነ-ጽሑፍም አፍቃሪዎች ነበሩ፤” ብለዋል (አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ የካቲት 8 ቀን 1960 ዓ.ም፤ ገጽ 5) ፡፡  አይንስታይንም ሆነ ዶክተር ኒኮላ ቴስላ በጥበባዊ ሙዚቃና ሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪነታቸው የታወቁ ነበሩ፡፡ በሃገራችንም ቢሆን ጥልቁና ረቂቁ ፍልስፍና የገባውና የኖረው በዜማና በቅኔ አማካኝነት ነው፡፡ በሙዚቃ የተራቀቁት ሊቃውንት - በዜማ ቤት፣ በቅኔ ቤትና መጽሐፍት ቤት ውስጥ ሚስጢራትን አቀላጥፈው የሚያውቁ ምሁራን ስለነበሩ ምናባቸው ሰፊ፣ ሥነ-ሥርዓታቸውም ሥልጡንና የተገራ ነበር (ኃይለ ገብርኤል ዳኜ፤ 1970፣ ገጽ 89-90)፡፡ የዜማ ቤት በአራት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው ድጓ ቤት ነው፡፡ ዓመቱን ሙሉ በቅዳሴና በሰዐታት ጊዜ የሚዘመ...

ከስፖርቱ ዓለም

ምስል
ጃፓናዊያን ሴቶች በፍቅር ያበዱለት የማራቶን ጀግና                                             በ ፍስሃ ተገኝ *************************************************** በአንድ ወቅት ጃፓናውያን ሴቶች አብረውት ለመሆን በቁጥር አንድነት የሚመኙት ጎረምሳ ነበር። እሱ ያለበትን ሁኔታ በንቃት ይከታተላሉ፣ ባዩት ቁጥር በደስታ ይጮሀሉ። ስለ ብራድ ፒት ወይም ዴቪድ ቤካም እያወራሁ አይደለም፤ ስለ አበበ ቢቂላ እንጂ። እ.አ.አ በ1961 ዓ.ም በጃፓኗ ኦሳካ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ተሳትፎ  በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ በጃፓናውያን ሴቶች ልብ ውስጥ መግባት የጀመረው አበበ ቢቂላ በ1964ቱ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ወደጃፓን ሲሄድ በሰውነት አቋማቸው ከሚበልጡትና በእድሜ ከሱ ከሚያንሱት ፈርጣማና ጡንቸኛ አሜሪካዊን የኦሎምፒኩ ተሳታፊዎች ቦክሰኛው ጆን ፍሬዠርና ዋናተኛው ዶናልድ አርቱር ሾላንደር ይልቅ የሀገሪቷን ሴቶች ቀልብና ልብ መስረቅ ችሏል። እ.አ.አ በ1932 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ጃቶ ውስጥ የተወለደው አበበ፤ ከእናቱ ጋር ለመኖር በሚል የትውልድ ቦታውን ትቶ ወደ አዲስ አበባ ከሄደ በኋላ በቅድሚያ ከከተማዋ የወደደው ነግር ቢኖር ጥርት ያለና ስርአት ያለው የደንብ ልብስ የሚለብሱት የአጼ ኃይለ ስላሴ ክቡር ዘበኛ አባሎች ነው። እና...

ኪነ ጥበብ

ምስል
ፊልም፣ "ሰባተኛው ስነ-ጥበብ" በሰሎሞን ተሠማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com) የአንድ ሀገር ህዝብ በጦር ሜዳ ግንባር የመጣበትን ወራሪ ጠላት መክቶ በድል አድራጊነት ቢወጣ ባለድል መሆኑ እሙን ነው፡፡ ድሉ በወታደራዊው ጦርነት የመጨረሻውን ትግል አድርጎ ለማሸነፉ ምስክር ነው፡፡ በባህሉና በማንነቱ በኩል ግን የሚመገበው፣ የሚለብሰውና የሚነጋገርበት ዘዬ፣ ወራሪዎቹ ትተውት የሄዱትን ርዝራዥ ብኂል ነው፡፡ ጦርነቱ ብርቱ ብርቱ የጦር አበጋዞችን እንጂ፣ ቆራጥ የባህል ጠበቆችን ወይም ስለባህልና ስለሥነ-ጥበብ ተምረው የተዘጋጁ ኃይሎችን (ልሂቃን) ስላላዘጋጀ፣ ከፍ ያለ የጥበባዊ ሽንፈት ይከተላል፡፡ የባዕዳንን ርዝራዥ ባህል በሲኒማና በመዝናኛ ውጤቶች እየተመገበ የሚያድግ ወጣት እንደምን አድርጎ የራሱን ታሪክ ሊተርክ ይችላል? እንዴትስ የራሱን እሴቶች ዋጋ ሊሰጥ ይችላል? ስለሆነም ወጣቱ   የውንብድናና የወላባነትን ባህሪ ብሂሉ ያደርገዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ፣ የቬትናም፣ የላቲን አሜሪካንና የበርካታ የመካከለኛው ምስራቅ አገር ሕዝቦች የጦር ሜዳ ወራሪዎቻቸውን በወኔ ቢመክቱም ቅሉ፣ የወረራቸውን የምዕራባዊያን ባህል ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም፣ ኤድዋርድ ሳይድ፣ Orientalism በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ እንዳተተው፣ “መሪዎቹና ሕዝቡ ሙሉ ኃይላቸውን ጦርነቱ ላይ አድርገውት ስለቆዩ፤ ታሪካቸውን፣ ባህላቸውንና ማንነታቸውን በዝንጓዔና በቀልበ-ቢስነትም ስለሚዘነጉት ነው” ይላል፡፡     ኢትዮጵያዊያንም የአድዋንና የአምስቱን ዓመት የፀረ-ወረራ ትግል ካካሄዱ በኋላ ታሪካቸውንና ባህላቸውን እንዲዘነጉ የጣሊያን ወራሪዎችም ሆኑ ቆንስላዎቹ ያልተቆጠበ ጥረት አድርገዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሥርግው ኃብለ ሥላሴ “ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ፣ የአዲሱ...

ከመጻሕፍት ዓለም

ምስል
“ዣንቶዣራ” ዓይናችንን የገለጠልን ልብወለድ!  በእርግጥ የቀዳሚ እና የተከታይ ደረጃ ለመስጠት ያዳግተኛል፡፡ ይስማዕከ ግን በአማርኛ ልብወለድ ውስጥ ከተለመደው አብራሪነት፣ ገላጭነት፣ (ለምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩም እንደሚተቸው ቀኑ ደመናማ ነው ሰማዩ ብልጭ ድርግም ይላል…) እያልን ከምንወርድበት ዘልማዳዊ ጥንወት መንጭቆ ሊያወጣን ይታትራል፡፡ የ”ዣንቶዣራ” ቁጥር አንድ እምርታ ሁነትን ከማብራራት እና ከመተረክ ይልቅ በገጸ ባሕርያት አማካኝነት የሰላ ትችትን መሰንዘር፣ ጥልቅ ፍልስፍናን መወንጨፍ፣ የሕዝቡን ብሶት ማስተጋባት ወዘተ. ነው፡፡ በህዳሴ እንቅስቀሴአችን ውስጥ ያላየነውን እናይ ዘንድ (ግልብ ስልጣኔአችንን እየገለበ) የሚሞግተው ኪራኮስ በተባለ ገጸ ባሕርይ አማካኝነት ነው፡፡ እርጅና ያልሆነ ሰንፍና ካልተጠናወተኝ በስተቀር አስታውሳለሁ! ከአንድ ድፍን ዓመት በፊት መጽሐፍ እያሳተሙ ከደራሲ ወገን የሚሆኑ ሰዎች እንደመብዛታቸው ፖለቲካችንን እና የአስተዳዳሪዎቻችንን የአስተዳደር ዘይቤ የሚደፍር ትጉህ ብዕረኛ እምብዛም እንደሌለ ጽፌ ነበር፡፡ በዚህኛው ጋዜጣ አልነበረም፡፡ ያኔ በዕውቀቱ ሥዩምን ስለፖለቲካዊ ሽሙጡ፣ ይስማዕከ ወርቁን ስለ የሀገር ፍቅር ቀስቃሽ ጽሑፎቹ መጥቀሴን ግን ኮራሁበት፡፡ ዴርቶጋዳን ለአንባቢዎቹ ባቀረበ ጊዜ የንባብን አብዮት በኢትዮጵያ ላይ የለኮሰው ይስማዕከ ወርቁ ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ መዳበር፣ መታተም፣ መነበብ የራሱ የሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል፡፡ “ዴርቶጋዳ”ን ነግደው የከበሩ መጽሐፍ ሻጮችንም ሳንዘነጋ! በተከታታይ ያሳተማቸውን መጽሐፎቹን ብዙዎቹ በጉጉት ሲሻሟቸው አስተውለናል፡፡ በቅርቡ ያወጣው አምስተኛ ልብወለዱ ሲሆን ግጥሞቹን ስንጨምር ሰባተኛ መጽሐፉ መሆኑ ነው፡፡ የአሁኑ መጽሐፉ “ዣንቶዣራ” ይ...

ሞክሼ የአማርኛ ፊደላት እና የባለሙያዎች ማብራሪያ

ምስል
ክፍል አንድ የፊደል ዘር ይጠበቅ ባህሉም ይከበር በፊታውራሪ አበበ ሥዩም ደስታ በፊደሎቻችን ላይ ሦስት ሀ - ሐ - ኀ፣ ሁለት አ - ዐ -፣ ሁለት ሠ - ሰ ሁለት፣ ጸ - ፀ አሉ፡፡ እነዚህ ፊደሎች የራሳቸው የሆነ የስም አጠራርም አላቸው፤ ሀሌታው ሀ፣ ሐመሩ ሐ፣ ብዙኃን ኀ፣ ንጉሡ ሠ፣ እሳቱ ሰ፣ ጸሎት ጸ፣ ፀሐዩ ፀ ይባላሉ፡፡ በጽሑፍ የሚገቡበትን ተገቢ (ተስማሚ) ቦታም አላቸው፡፡ ለምሳሌ በሁለት ፊደሎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ሀገር አገር ይህ ትክክለኛ አጻጻፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ሐገር፣ ኀገር ብሎ መጻፍ ግን ስሕተት ይሆናል፤ የሚከተሉትን ደግሞ እንመልከት፤ ሕገ መንግሥት፣ ሕገ ወጥ፣ ሕዝብ፣ ሕብረት፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ወዘተ. የመሳሰሉት አጻጻፋቸው ትክክል ነው፡፡ ከዚህ ልማዳዊ አሠራር ውጪ ህገ መንግሥት፤ ህገወጥ፤ ህዝብ፤ ህብረት፤ አቃቤ ህግ ስሕተታዊ አጻጻፍ ይሆናል፤ ሌላ ማስረጃ ቢፈለግ፤ ኃይለሥላሴ የሚለው ስም ሦስት የተለያዩ ፊደሎች ይዟል፡፡ የመጀመርያው ፊደል ብዙኀን - ኃ - ሲሆን፣ ከንጉሡ -ሥ- ሳድስ፣ ከእሳቱ -ስ- ሃምስን በመጻፍ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ ሀይለ ስላሴ ብሎ ቢጻፍ ግን የፊደሎቻችን የአጻጻፍ ሥርዓት ማፋለስ ይሆናል፤ በአቦ ሰጡኝ ፊደሎቻችን አለቦታቸው መግባትም፣ መጻፍም የለባቸውም፡፡ በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር የነበሩት የተከበሩ ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ የቅድሚያ ዓይነተኛ ሥራቸው የፊደሎች ዘሮች አለቦታቸው እንዳይጻፉ መጠበቅ ነበር፤ በዚያን ወቅት ተማሪ ሁኜ አልፎ አልፎ በጋዜጣ እንዲወጣልኝ አንድ አንድ ሐሳብ በማመንጨት እጽፍ ስለነበር ብዙ ጊዜ አርመውኛል፡፡ ከእሳቸው በተማርኩት ትምህርትና ባገኘሁት ልምድ አእምሮዬን አሻሽያለሁ፡፡ በቀ...

ተፅዕኖ ፈጣሪው ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ

ምስል
“ሰውን ሰው ቢወደው አይሆንም እንደራስ ታመህ ሳልጠይቅህ መቅረቴን አትውቀስ ባውቀው ነው የመጣሁ እንደማልመለስ ይማርህ መሀሪው እስመጣ ድረስ” /ዮፍታሄ ንጉሴ በቅድመ ፋሺስትና  በድህረ ወረራ በርካታ ስራዎቻቸውን  አበርክተው ላለፉት ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ስላሴ  ህልፈት የጻፉት የሀዘን እንጉርጉሮ ነበር፡፡/ “ጎነዛዚቴ ሆይ ወይ ቆነጃጅቴ ምንኛ ነደደ ተቃጠለ አንዠቴ እንመለሳለን ባዲሱ ጉልበቴ እናንተም ተምርኮ እኔም ተስደቴ” *************************************************************************** የአማርኛን ስነ ጽሁፍ ካሳደጉት ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን መካከል ባለቅኔው ዮፍታሄ ንጉሴ ይጠቀሳሉ፡፡ ዮፍታሄ ንጉሴ የተወለዱት በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረ ኤልያስ በ1885 ዓ.ም ሲሆን በደብረ ኤልያስ ደብር የጥንቱን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትምህርት በሚገባ ተምረዋል፡፡ ዮፍታሄ በልጅነታቸው የዜማ ትምህርት ያስተማሯቸው መሪጌታ አደላ ንጉሴ ሲሆኑ የቅኔን ትምህርት ያስተማሯቸው የኔታ ገብረስላሴ ነበሩ፡፡ የኔታ ገብረስላሴ በደብረ ኤልያስ ደብር ታዋቂ የቅኔ መምህር ሲሆኑ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስን ቅኔ እንዳስተማሯቸው በታሪክ ይታወቃል፡፡ ደብረ ኤልያስ ደብር የ”ፍቅር እስከ መቃብር” ደራሲ ሃዲስ አለማየው የተማሩበት ደብር ነው፡፡ አቶ ሙሉጌታ ስዩም በ1964 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዩኒቨርስቲ በመመረቂያ ጽሁፉ ላይ እንደገለፀው፤ በደብረ ኤልያስ ደብር የነበሩ መምህራን “ማህበረ ኤልያስ” በሚል ስም እግረ ኤልያስ ብለው ደቀመዛሙርት ተማሪዎቻቸውን ይጠራሉ፡፡ በዮፍታሄ የዜማና የቅኔ ችሎታ መምህራኖቹ ከመደነቃቸው የተነሳ ለአምስት ተከታ...

የሸገር ሬዲዮ መዓዛ

ምስል
 ክፍል --፪ ************** እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የሬዲዮ መቀበያችንን መስመር በኤፍ ኤም በኩል ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ ብንዘውረው ሰባት ያህል የሬዲዮ ጣቢያዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡ ሬዲዮ ጣቢያዎቹ የተለያዩ ቢሆኑም አብዛኞቹ የሚያቀርቡት ተመሳሳይ “ዝግጅት” ነው፡፡ አንዱን ጣቢያ ከሌላው ለመለየት የሚያስችል የራሳቸው የሆነ መለያ ቀለም ስለሌላቸው፤ የአንዱ ሬዲዮ ፕሮግራም በሰባት የሬዲዮ መስመሮች ውስጥ ተከፋፍሎ የሚሰማ እስኪመስል ድረስ ምንም ዓይነት ልዩነት አይታይባቸውም፡፡ የሚያቀርቧቸው ፕሮግራሞች በክሊሼ የታጀሉና ኦና ከመሆናቸው የተነሳ አድማጭን ያንገፈግፋሉ፡፡ መስፍን ሀብተማርያም በአንድ የወጐች መድበሉ ላይ እንዳለው፤ ለአንዳንዶቹ ሬዲዮኖች ሲባል “ምነው ጆሮም እንደ ዓይን ቆብ በኖረው” ያሰኛል፡፡ ለመሆኑ ጥሩ የሬዲዮ ፕሮግራም እንዴት ያለ ነው? ጥሩ የሬዲዮ ፕሮግራም፤ ባለሙያ መጥናና ቀምማ ባሰናዳችው መልካም ወጥ ሊመሰል ይችላል ይባላል፡፡   የባለሙያዋን ቅመም ዓይነትና መጠን እንዲሁም የአበሳሰል ዘዴ ባናውቀውም፣ በማድመጥ ግን ጥሩው የቱ እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡ ለምሳሌ ለእኔ መልካም የሬዲዮ ፕሮግራም ማለት እንደ ቢቢሲ፣ እንደ ዶቼ ቬሌ፣ እንደ ቪኦኤ ወይም እንደ ሸገር ሬዲዮ ፕሮግራም ያለ ነው፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት የማያቋርጥ መሰናዶ እንደሚሻ የዘርፉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም ሙያው ከማንኛውም የጋዜጠኝነት ዘርፍ ያላነሰ ምርምር፣ ሐቀኛ መረጃ እና እንደ ጥበብ ደግሞ የፈጠራ ሥራ ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ላይ ተመስርቶ ቀላል፣ የተመጣጠነ ሆኖም አዝናኝ ወይም አስተማሪ የሆነ ፕሮግራም ከሙዚቃ ጋር ተዋህዶ ለዛ ባልተለየው ዘዴ ሲቀርብ የአድማጩን...